እሺ አሁንስ ባህር ዳር ላይ ደግሞ ወገኖቼን ለምን ገደላችሗቸው? ዳዊት ዳባ
የባህር ዳር ህዝብ ይህን ቦታ እጅግ ለረጅም አመታት ለአምልኮ ስንጠቀምበት የነበረ ነው። ለባለ ሀብት መሰጠቱና ለሌላ አገልግሎት እንዲውል መወሰኑ ትክክል አይደለም ብሎ ቅሬታውን ሊያሰማ አደባባይ ወጣ። ይህ ለእምነቱ የሰናፍጭ ቅንጣት ታህል ቀናዊ የሆነ በአገሬ ጉዳይና በኑሮዬ እሚንት የምታህል መብት አለኝ ብሉ የሚያስብ የየትም አገር ዜጋ ሊያደረገው የሚችል ነው። በእውን ይህን ማድረግ የሚከለከል ወይ ማድረጉስ ወንጀል የሚደረግበት ህዘብ በአለም ላይ አለ ወይ?። እኔእይመስለኝም።
በዋናነትቅሬታቸውን ሰልፍ ወጥተው ማሰማታቸው የህግ አግባብ ያለው ነው። ህዝብ ይህን ማድረጉ ተፈጥራዊም ህገ መንግስታዊም እምነታዊም መብትመሆኑ ደምቆ ይሰመረብት። ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ቅሬታቸውን ማቅረባቸውንም እንዲሁ።
ይህም ሆና በባህር ዳር ላይ የሆነው እጅግ እጅግ በጣም ቀላል ነገር ነበር። መገድል መደብደብ ማዋከብ ውስጥ ሳይገባ ይህን የህዝብ ቅሬታ ማስተናገድ በቀላሉ የሚቻልባቸውመንገዶችነበሩ።የሚያዳምጥ አካል በመላክ ቅሬታውንማዳመጥን ብቻ ነበርእኮ የሚፈልገው።የህዝቡ ቅሬታ እውነታ ከሌለው እውነታውን ማስረዳት። የህዝቡ ቅሬታ እውነትነት ኖሮት ቦታው ለሌላ አገልግሎት ተሰጥቶ ከሆነ ውሳኔው የተላለፈበትን አግባብና በልዋጭ ህዝብ አምልኮውን የሚፈፅምበት ቦታ ተዘጋጅቶ ከሆነ ይህንን መንገርና በቀላሉ ሰላማዊ ፍፃሜመስራት ይቻል ነበር። ሌላ ሶስተኛ አካል ከጀርባ ህዝብን አሳስቷል። ነጭየገዳዬች ምክንያት ነው።ካልሆነ ከጨፈጨፍክ በሗላ ሳይሆን እዛው ሰልፉ ላይ አሳስተዋችሁ ነው። የምታቀርቡት ቅሬታ ምንም መሰረት የሌለው ነው። በማለት የተፈጠረውን አለመግባባት ማጥራት አይቻልምነበር ወይ?። ቅሬታው አግባብ ኖሮት ውሳኔው የተላለፈበትን አግባብ እዛው መንገሩ ጥሩ አይሆንም ተብሎ ከታሰበም። ቅሬታውን አድምጠናል።መልሳችንን በዚህ ቀንበዚህ መንገድ እንሰጣለን ማለትንስ ማንን ገደለ።አዎይህን በማድረግበሰለጠነው መንገድ መጨረስ ስትችሉ ፈጇችሗቸው።
ሁላችንም ማወቅያለብን እንደሁሌውይህ እጅግ ቀላል ነግር በዚህ አይነት አሳዛኝ ሁኔታ የተፈፀመው አምጠንምሰበብ ልንወልድልት በማይቻለንስልጣን ላይ ያሉት የትግሬ ወያኔዎችበመሆናቸውነው። አንድነት፤ ሰማያዊ፤አዎ ኢሰፓም ብቻ የትኛውም አካል ስልጣን ላይ ቢሆን ኖሮ የሚያደርገው ካላይ ያልኩትን ነበር። በእርግጠኛነት የምናገረው ለዚህ ቀላል ነግርየሰው ልጅ ለዛውም ዜጋ አይደለም ዝንብ አይሞትም ነበር።እናንተ ግን በምታውቁትናሁሌም የዚህ አይነት የህዝብ ቅሬታን በምታስተናግዱበትመፍጀት በእድሜ የጠገቡ አሮጊቶችንና ለአካለ ስንኩላን እንኳ ሳትራሩ ዘግናኝ ወንጀል በድጋሚፈፀማችሁ። ግን ለምን?። ለምን ለሰው ለጅ ለዛውም ለወገናችሁ ሂወት የምትሰጡት ክብር እዚህ ደረጃ ወረደ?።ህዝብን ማሸበር እንዴት ነው እንደዚህ ደስታን እየሰጣችሁ ያለው?።ጎበዝ ግርም የሚል ነገር እኮ ነው የገጠመን።
ይህ በመፍጀት የሚነሱ የመብት ጥያቄዎችንና ቀላል ቅሬታዎችን ሁሉ መፍታት ለሀያ ሶስት አመት ሙሉ በተደጋጋሚ ሲፈፀሙየነበረ መሆኑን ልብ እንበል። ሚሊዬኖችንቀጥቅጠውበታል። በመቶ ሺዎች ገድለውበታል። በመቶ ሺ ዎች በየማጎርያው የመከራ ሂወት እንዲገፉበትአድርገዋል። ሚሊዬኖችን አሰድደዋል። ብዙዎችን ያለወላጅ አስቀርተዋል። ይህ ግፍ የተፈፀመባቸው ብዙዎቹ ይህን አይነቱን በሽታ ዝም ስለተባለማቆሚያ የሌለው መሆኑን በጠዋቱ አውቀው አቁሙ ስላሉ መሆኑን ደግሞ አንዘንጋ።
ዛሬም የሆነ አይነት “መንግስት” አድራጋችሗቸው ህግና ስርአትን ከማስከበር አኳያ፤እንዲሁም በአደባባይ ስሜትን ለመግለፅ ከማሳወቅ በሉት ከማስፈቀድ የህግ አግባብ አኳያ እያያችሁ ትርጉም እንዲሰጣችሁ እየጣራችሁ ያላችሁ ትኖራላችሁ። እውነት እውነት እላችሗለውበጣሙን ተሳስታችሗል።እሩቅ ቦታ ሳልሄድ ሀዘን ደስታ ንዴት የስሜት ጉዳዬች ናቸው። ሁሌበቀጠሮ የምናደርጋቸውአይደሉም። የሄን ደግሞ እኔ ስላልኩ አይደለም።ወያኔዎችም ያውቃሉ። ብሄራዊ ቡድናች ሌላ ጊዜ ደግሞእሯጮቻችንአሸነፉ ብሎ ይህው ህዝብበብዙ ቁጥር በደስታ ስሜት ብዙ ጊዜ ሳያስፈቅድ አደባባይ ወጥቷል። ገደሉት?። አልገደሉትም። ጦርነት አሸነፍን ባድሜ ለኛ ተወሰነ ብሎ ደስታውን ለመግለፅ ህዝብ አደባባይ በብዙ ቁጥር ወጥቶ ነበር።ፈጅት ፈፀሙበት?። አልፈፅሙም። መለስ ሞተ ብለው ሀዘኑን ሊገለፅ ነውብለው ያለ ምንም ፍቃድ አሁንም አደባባይ ያወጡትን ህዝብ ፈጁት?። አልፈጁትም።እነሱ ደስታቸውን፤ ዝክራቸውንና ስኬታቸውን ሊነግሩን የበዛውን ጊዜ አደባባዩን የሚጠቀሙና ሲሰበሰቡ የሚውሉ ናቸው። እያስፈቀዱ ስለመሆኑ የምታውቁት ነገር አለ?። አስፈቀዱ ወይ ተከለከሉስ ሲባል ሰምታችሁ ታውቃላችሁ?። ወይ እዚህ ቦታ መሰብሰብ ወይ መሰለፍ አትችሉም ተባሉስ ሲባልስ?። ሲቀሰቅሱ አባላትታሰሩባቸውስ ሲባል ሰምታችሗል?። አውቃለው ጥያቄዬ የሞኝ እንደሚመስል። የማነሳው ግን ህጋዊነት ላይ ጠንካራ እምነት አለችሁና እነሱ ከህግ በላይ ናቸው እንደማትሉ ገምቼ ነው።
ወያኔንና ወንጀሎቹንና ጥፋቶቹን በሚመለከት ተሳስታችሗል ስላልኩ አይክፋችሁ። ይህን ለጉድ የገነነብንን ድርጅት በሚመለከት ማንም ሁሌ በሁሉ ነገር ትክክል ሆኖ አያውቅም። ሁሌትክክል መሆንም ለማንም ቀላል አልሆነም። በዙ ጊዜ የህዝብ ስህተተኛነት ከጨዋነትና አርቆ ከማሰብም እንደሚመጣም አሳምሬ አውቃለው። ደጋፊዎቹን እንተዋቸውና ወያኔዎችን በብዙ ድምር ምክንያቶች መሰረት አድርጎበጭራሽ የማይፈይድና ጎጂ ቡድን ነው። ለመልካም በቶሎ መጥፋት አለበት ብለን ያሰመርን ብዙዎች አለን። በሌላ ወገን ደግሞ በእምነቱ ለመቆየት የሚያያቸውንና የሚሰማቸውን አስገራሚ፤ዘግናኝጥፋቶችና ወንጀሎችን በሙሉ በሚቻለው ሁሉአመክንዮ ሊሰራባቸው፤ትርጉም እንዲሰጡትሲጥር ሲጥር የሚኖር አለ።ምክንያታዊ ለመሆን ከእለት እለት እየከበደውና እጅጉኑ እየተቸገረ ያለቢሆንም ተስፋው ፈፅሞ ያለተሟጠጠ ወይ እንዳይሟጠጥ እየጣረ ነው።ይህ ክፍል ብዛቱቀላል የማይባል እንደሆነምይታወቃል። ወያኔዎችን በሚመለከት ሁላችንም በሁሉ ነገር ሁሌ ትክክል ለመሆን ይከብደናል ስል ግን በሁሉም ወገን ያለነው ስህተት ስለምንሰራ ነው። የኔን በሰሞኑ የተገለፀልኝን ደደብ የነበረ ስህተት ልንገራችሁ።
በጠኔ ለሚሰቃይና ልጆቹን መመገብ ለቸገረው ብዙ ሚሊዬን ህዝብ እርቦናልሲላቸው ጠግበሀል ብለው ሲከራከሩት እሰማለው። አንዷለም እስክንድርና፤ ዞን ዘጠኞችን አሸባሪ ስለሆኑ ነው ብለው ሲከራከሩ እሰማለው። ቦንብ አፈንድተው ገድለው እነንትና ናቸው ብለውሲከራከሩን እሰማለው። ቤተሰቦቻችንን ሰብስበው ልጆቻችሁን አሁን እንገላለን ወይ ልንገላቸው አምሮናል ሲሉና ሲደነፉ እሰማለው። እነዚህ እንደው ለምሳሌ ነው ያቀረብኳቸው።ሁሌና ሁሉ ነገራቸው አስገራሚ ድርቅና ያለበት፤ አሳማኝናአግባብ ያለው እንዲመስል እንኳ ቅንጣት ታክል የማይጨነቁበት እንደሆነ አውቃለው።የበዛ ድፍረትም አይባልም ጥጋብ ያለበቻውመሆኑን አውቃለው። በዚህ ደረጃ ነውእየተረዳሗቸው ነው እንግዲህ። እንደዚህ የሚያደርጉት ለምንድን ነው?። ለሚለው ጥያቄ መልስ ለመስጠት ስሞክር የተሳሳትኩት።
የሚመስለኝ የነበረው ከጠቅላላ የመሀበረባችን ግንዛቤ፤ የድህነቱ ደረጃ፤የበዛው ዜጋ ከነሱ ወገን የሚቀርበውን መረጃ ብቻ ስለሚያገኝ፤ ያልቆረጠለትና እንዲቆርጥለት የማይፈልገው ዜጋ ገና ብዙ ቁጥር ያለውስለሆነ። ምንም ብንለው ሀሳቡን የገዛዋል ከሚል ነውአይነት ምክንያቶችን እደረድር ነበር። የሚመስለኝ የነበረው እነዚህንና የመሳሰሉ ነገሮች በጥልቅ አስበው፤ አይተውትና አስልተው፤ ሌሎች መንገዶች መኖራቸውን ቢያውቁም ላሁንመፍጀቱ መቀጥቀጡና ማሰሩ ይሻላል፤ያዋጣልም፤ሰርቷልም ብለው በማወቅ የሚያደርጉት ነበር የሚመስለኝ።ስህተቴን ያሳየኝ በሰሞኑ በስዊድን ዜጎች ላይ ያደረጉት የመግደል ሙከራና እንግሊዛዊ ዜግነት ያለውን ግለሰብ መግደላቸው ነው። ለምን የነዚህ አገር ዜጎች እንደተመረጡ ማወቁ አልከበደኝም። ለምን መግደሉን መረጡ ለሚለው ጥያቄ ግን ከዚህ በፊት የምደረደርውምክንያቶች አንዳቸውም በጭራሽእንደማይሆኑ ተረዳው። እስከዛሬም ስህተቴ አለማወቅ ብቻ ሳይሆን እውነቱን ለማመን አለመፈለግ [Denial] እንደነበረበትም አወኩ። ምን ላድርግ ስልጣን ላይ ያለን አካል በዚህ ደረጃ ለማወቅ የሚያስፈራ ነገር አለው።
ለማንኛውም ይህን በሽታ ዝም ብለን እንዲቀጥል አናድርገው።በጭራሽ አይቆምም። በአንክሮ ላጤነው በፈጠነ ሁኔታ እየጨመረእየባሰበትእየሄደ ነው።ብዙ ልናደርጋቸው የምንችላቸው ነገሮች አሉ። ልናደርግ የምንችለውን የምር አድርገን ልናስብበት ግንእንጀምር።ላሁኑ የተቃውሞ ሰልፎች ታቅደዋል እንቀላቀል። ሁላችንም ልናደረገው የምንችላቸው ቀላል የሆኑ ነገሮች ደግሞ ብዙ አሉ። እነዚህን አንዳኗም ሳናስቀር ሁላችንም ዛሬ ማድረግ እንጀምር። አሁንለምሳሌ እድሜያችሁ ለመምረጥ የደረሳችሁ በሙሉ ማድረግ የምንችለው ስለሆነ እባካችሁ ሄደን የመምርጫ ካርዳችንን አሁኑኑ እንውሰድ። የተለያየ አመለካካት ምርጫው ላይ ሊኖረን ይችላል። ቅንጦት ቢኖርበትም ይህ ችግር አይደለም። ልዩነቱ ላይ መጨቃጨቁ ይቀጥል። ማወቅ ያለብን አገዛዙ ምርጫ አለ፡፤ ውጡና ምረጡ ብሎን ይህን ማድረጋችን ደግሞ የሚረብሸውና የሚያስጨንቀው መሆኑን ነው።ደግሞ ፍራቻው ምክንያታዊም ትክክልም ነው።ሁላችንም ከተመዘገብን ምርጫ የሚባለው ነገር እራሱ ቀርቷል ሊሉ ወይ ካርድ ሊያወጣ የተሰለፈ ህዘብ ላይ ደግሞ ልተወው።ብቻትግል ብለን ካደረግነውትግል የማይሆን ምንም እስከጭራሹ ምንም ነገር የለም። እስቲ ነገ ፖሊሱንም፤ ወታደሩንም፤ደህንነቱንናካድሬዎችን በተለየ ሁኔታ ሞቅ አድረገን ፈገግታ መስጠትና ሰላም ማለት ሁላችንም እንጀምር።ድርጊታችንን ትግል ነው እንበለው።በእርግጠኛነት በነጋታው መሳቅ ከአሸባሪነት ጋር ተያይዞ በኢቲሺ ሲተነትኑበት ትሰማላችሁ። ቆያይቶ ደግሞ ማግጠጥ ይባልና ህገ መንግስትን በመናድ የሚል ህግ ተጠቅሶበት እስር ቤት የሚገባ ይኖራል። ብቻ ዝም አንበል።በሆነ መንገድበግፍ ለገደሏቸው ወገኖቻችንመቆርቆራችንን እናሳይ። ላሁኑእንጠራራ፤እንሰባሰብ፤እንቀሳቀስሄደንከርዳችንን በእጃችንእናስገባ። የተቃውሞ ሰልፎችን በገፍ ወጥተን እንቀላቀል።
የሞቱትን ነብስ ይማር። መፅናናቱንና ጥንካሬውን ለሁላችንም ይስጠን።