በአስመራ የመሸጉ ተቃዋሚዎች እና የሻእቢያ ግፍ
በአስመራ የመሸጉ ተቃዋሚዎች እና የሻእቢያ ግፍ
አንደኛ – በሻእቢያና በወያኔ ልዩነት የለም ፤ ጠባቸው በራሡ ሻቢያ ወያኔን አንስቶ በሌላ ትግሬ መተካት ይፈልጋል እንጅ ከወንድሞቹ "ትግራዋይ" ጋር ምንም ፀብ የለውም ደምህት የሚባለው የትግሬ ድርጅት ባጭር ጊዜ የት እንደደረሰ ማየት ይቻላል፤ ወያኔም እንደዛው ምንሊክ ነው ከወንድሞቻችን የለየን እያሉ እየነገሩን ነ።
ሁለተኛ ፦ ከደምሕት በአራት አመት ቀደም ብሎ የነበረው አርበኞች ግንባር አመራሮቹ ታስረዋል እንደውም ኮለኔል ታደሰን ሻብያ ገድሏቸዋል ።በርካታ የአርበኞች ግንባር አባላት ታስረዋል ትግሉን ጥለው ተሰደዋል:: በቅርቡ የአማራ ንቅናቄ የሚባሉት በኤርትራ ያለው ትግል የውሸት ነው በሻእቢያ ቤት ሆኖ ነጻነት የለም መውጣት አለብን ብለው ስላሉ አምስት አባሎቼን ሻቢያ አፈነብኝ ሲል ተሰምቷል፤ ልብ በሉ እንኳን መደራጅት በቃን ብለው ከኤርትራ መውጣት አልቻሉም ።
ሶስትኛ :- ግንቦት ሰባቶች ግልጽ የሆነ አድር ባይነት እያሣዩን ነው ፤ እነሱ የሚሉት እዛ የታሰሩት ከኢሳያስ ጋር ችግር ስላለባቸው ነው ይሉናል ። የምን ችግር ብለን አማራ ፎርስ የሚባሉትን ስንጠይቅ ሻእቢያ እንደህጻን ልጅ "ሁን" የሚልህን ከመሆን ውጭ እንዲህ አደርጋለሁ ማለት ፈጽሞ አይታለምም ይሉናል ። እውነት ነውም ። ግንቦቴዎች ግን ይህን ተቀብለው እየሰሩ ነው ። ልብ አድርጉ ኤልያስ ክፍሌ አስመራ የኢትዮጵያን ሪቪው ቅርንጫፍ ሊከፍት ከሻብያ ጋር ተስማምቶ ነበር ፤ የኮለኔል ታደሰን መታፈን እንደሚቃወም ስለጻፈ ብቻ ከሻእብያ ጋር ተጣልቷል ፤ ኢሳት ኤርትራ ውስጥ ስለሚደርሰው ሰቆቃ ሲዘግብ ሰምታችሁ ታቃላችሁ ? አይችልም ። አንዱ የሚረዳው ሻእቢያ እንደሆነ የዶክተር ብርሀኑን ድምጻቸውን ሰምተናል (የሚረዳው ሲባል ለድርጅቶች የሚገባው ገንዘብ መጀመሪያ ሻእብያ ላይ ነው ፣ ያኑ ገንዘብ ነው የሚስጣቸው እሱ የፈቀደውን እና እንዴት ነው ኢሳትስ አለቃየ ሻእብያ ይሄን በደል ሰራ ብሎ የሚናገረው ?)
ልብ ያለው ልብ ይበል ሻእብያ ወያኔ ቢጠላ ኢትዮጵያን ወደደ ማለት አይደለም ። ወያኔም እንደዛው ። ሻእብያ ትናንት ኢትዮጵያን የመቶ አመት የቤት ስራ ስጠሓት ብሎናል ። መቸም ቢሆን ኢትዮጵያን አይወድም ። አትልፉ ። ለምን አርበኞችና ግንቦት ሰባት አልታጠቁም ደምሒት ባጭር ጊዜ ካሥር ሺ በላይ ሰራዊት አለው ። ሁለቱ 500 የሚሆን ታጣዊ አላቸውን ? ይሄ ሆን ተብሎ በሳይካተሪስቶች የኢትዬጵያን ህዝብ ለዛላለሙ ልቡን ለመሥበር የተቀየሰ መንገድ ነው ። እንዴት እንደሚሆን ወደፊት የምናየው ነው ።
ባሁኑ ስዐት ሻእቢያ ሀገር ያለው ነገር ፡ ወያኔ ኦሕዴድና ብአዴን ብሎ እንዳስቀመጣቸው ያሉ በደምሕት ስር ቅጥረኛ ሆነው ሊገቡ ያሰፈሰፉ ናቸው ። እነሱ የሚሉት ወያኔ ይውደቅ እንጅ ነው ፤ እውነታው ወታደራዊ መንግስት ሆኖ ነው የሚመጣው ከዚያ ቡሃላ ትግራይና ኤርትሬ "ፒስ" በሚል ቅኝ ግዛት ውስጥ ለዘላለሙ ትወድቃለህ ።
ግንቦቴዎችን ለመቃወም ምንም አልፈራም ምክኒያቱም አሥመራ የሚያሥገርፉት ኢትዮጵያውያንን ነው በተለይ አማራውን ፤ ድርጅቱ ለይሥሙላ ያማራ ነው ተብሏል ። ግንቦት ሰባት NAIVE ነው ፤ ዋለልኝ ከግንቦት ሰባት በጣም በጣም ላማራዎች ይሻላቸዋል ብየ እላላሁ ።ግንቦት ሰባት ከማንም ድርጅት ሲነጋገር ተሰምቶ አይታወቅም ከ FIRST OROMOዎች ጋር ብቻ እንጅ ። ከሌሎች ጋር መነጋገር የማይችሉበት ምክኒያት መሰረት ሥለሌላቸው ብቻቸውን በሜድያ ህዝብ አታለው መያዝ ስለሚፈልጉ ብቻ ነው ።ግንቦቴዎች የትም እንደማይደርሱ እስረግጬ ስነግራችሁ ህብረትሰቡን ግን ላንዴና ለመጨርሻ ጊዜ ኢትዮጵያዊ የሚባል ድርጅትን እርግፍ አድርጎ ተስፋ እንዲቆርጥ ያደርገዋል ።የሻእብያን ግንቦቴዎች ማሸነፍ የምንችለው ሜድያ ሲኖረንና አስመራ የሚሰራውን ግፍ ማጋለጥ ስንችል ብቻ ነው ።