ሰበር ዜና – ሁለት የኢትዮጵያ አየር ሀይል ኤም አይ 35 ሄሊኮፕተር አብራሪዎች የሚያበሩትን ሄሊኮፕተር ይዘው ጠፉ
ሁለት የኢትዮጵያ አየር ሀይል ኤም አይ 35 ሄሊኮፕተር አብራሪዎች የሚያበሩትን ሄሊኮፕተር ይዘው ጠፉ።የት እንደገቡ እስካሁን አልታወቀም።
ለኢሳት በደረሰው መረጃ የ ኤም አይ 35 ተዋጊ ሄሊኮፕተር አብራሪዎቹ ሻምበል ሳሙ ኤል ግደይ እና መቶ አለቃ ቢልልኝ መኮንን ትናንት ጧት ለልምምድ እንደወጡ ነው ጠፍተው የቀሩት።
አብራሪዎቹ ከ 30 ደቂቃ በላይ እንዲቆዩ ከማይፈቀድላቸው የበረራ ራዲየስ በመውጣት የሚያበሯቸውን ተዋጊ ሄሊኮፕተሮች ይዘው መጥፋታቸው ተረጋግጧል።
ይህ ሪፖርት እስከተጠናቀረበት ድረስ አብራሪዎች የት እንዳሉ አልታወቀም።
ሁለቱ ከፍተኛ የ ኢትዮጵያ አየር ሀይል አብራሪዎች በስልጣን ላይ ያለውን ስር ዓት በመክዳት ከጎረቤት ሀገሮች በአንድኛቸው ሳያርፉ እንዳልቀረ ግምት አለ።
ኢሳት ዜና