ጠ/ሚ ኃይለማርያም፡- በዋነኛ ሰብሎች 250 ሚ. – ባጠቃላይ ከ300 ሚ. ኩ. በላይ ማምረት የቻለ አገር ሆኗል

* ‹‹በትጥቅ ትግልም የተሳተፈ፣ ዴሞክራሲ፣ ሰላም፣ ዘላቂ ልማትና እድገት እንዲመጣ ለማድረግ መስዋዕት የከፈለ ትውልድ አለ። ከእርሱ ትውልድ ተቀብሎ ደግሞ 2ተ ኛው ትውልድ ሥራ ጀምሯል።›› * ‹‹አንዳንድ ሀገሮች ያኔ 25 እና 30 ሚሊዮን እርዳታ ሲሰጡን ትልቅ እርዳታ ተደርጎ ነበር የሚታየው። ዛሬ እኛ የደረስንበት ደረጃ ሲታይ ደግሞ የህዳሴ ግድብን የመሰለ ወደ 4ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ ግድብ በራሳችን ለመስራት መጀመራችን…›› * ‹‹በቅርቡ የኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ፕሬዚዳንት በምንም ተዓምር ይህን ግድብ መጥቼ ማየት አለብኝ፣….እናንተ ለእኛም ሞራል ሆናችሁናል፣ ከእናንተ ቀጥሎ እኛም መስራት አለብን ብለው አቋም ይዘው ግድቡን መጎብኘት አለብኝ ብለው በተደጋጋሚ ጠይቀዋል፣ በቅርቡም መጥተው ያያሉ።›› * ‹‹በዘንድሮ ዓመት በዋና ዋና ሰብሎች የባለፈው ዓመት የዘንድሮን ሳይጨምር 2006 ዓመት ላይ ማለት ነው በዋና ዋና ሰብሎች 250 ሚሊዮን ኩንታል ተመርቷል፤ ከዚያ በላይ ደግሞ የስራስር ሰብሎች፣ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም ሌሎች የቅመማ ቅመምና ቅባት እህሎች፣ ቡና የመሳሰሉት ሲጨመሩበት ከ300 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ማምረት የቻለ አገር ሆኗል። ይሄ በህዝብ ቁጥር በሚከፋፈልበት ጊዜ ሀገሪቱ ራሷን በምግብ እህል መቻሏን ያስረዳል።›› – – – – –  አዲስ ዘመን፡- ሕገመንግሥታችን የአገራችንን የቁልቁለት ጉዞ ቀልብሶ የኢትዮጵያ ህዳሴ መሰረት እንዲጣል ያደረገ ነው ይባላል፤ ይህ ምን ማለት ነው? ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም፡ – በኢትዮጵያ ህዝቦች ከፍተኛ መስዋዕትነት ከተከፈለ በኋላ የኢትዮጵያን ህዳሴ ሊያረጋግጥ የሚችል ድል ተገኝቷል። ሕገ መንግሥታችን በዚህ ድል ላይ የተገነባ ሕገመንግሥት ነው፤ ከድሉ በኋላ የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና […]