የ‹‹መድረክ›› ሰልፍ እንድምታ
(ቢልልኝ ሀብታሙ አባቡ) የተቃዋሚዉ ጎራን በአንድ ሳምንት ውስጥ ሁለት አብይት ፖለቲካዊ ክስተቶችን አስተናግዷል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ ትግል ሲኮላሽ የመድረክ ደግሞ ቀዝቀዝ ያለ በሚመስል መልኩ ተስተናግዷል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ የሰላማዊ ሰልፍ ፕሮግራም በተስተጓጎለ በሳምንቱ የመድርኮቹ መሳካቱ ምን ሊያመላክት ይችላል የሚለውን ጥያቄ መሰረት በማድረግ የመድርኩን ሰልፍ ከራሱ ከመድርክ፣ ከመንግስትና ከህዝብ አንፃር ሊኖረው የሚችለውን እንድምታ አጠር ባለ መልኩ ለማየት እንሞክራለን፡፡ ሀ) ከመድረክ አንፃር መድርክ ከሌሎችና ፓርቲዎችና ከራሱም ያለፈ የትግል ልምድ የተማረው ነገር ያለ ይመስላል፡፡ ፓርቲው ቀድሞ ከነበረበት ጽንፍ ይዞ የመታገል አቅጣጫ በተወሰነ መልኩ ለዘብ እያለ መምጣት የሚያሳዩ ሁሄታዎችን መታዘብ ይቻላል፡፡ መድረክ ከሌጋሲው የተማረው ጉዳይ ቀድም ሲል በነበው ፅንፍ ይዞ የመታገል አቅጣጫ የመንግስትን የቁጥጥር ጫና እንዲሚያጠብቀው ሳይማር እንዳልቀረ ነው፡፡ በዚህም የተነሳ ባልተለመደ መልኩ ሌሎች ተቃዋሚዎች ክፉኛ የሚጥሉትንና መንግስት እየተጠቀመበት ያለውን ባንዲራ በሰልፍ ውስጥ መጠቀሙ በተወሰነ መልኩ ከአክራሪነት ለዘብ ያለ አቋም እያሳየ ለመምጣቱ ማሳያ ሊሆን ይችላል፡፡ ፓርቲው ወዶም ይሁን ተገዶ በወሳኝ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ከኢህአዴግ ጋር መመሳሰል ባይችል እንኳን መንግስት ከሚፈልገው የአቋም መለሳለስ ደረጃ ላይ ሊደርስ እንደሚችል የሚጠቁሙ ፍንጮች እንዳሉ መውሰድ ይቻለላል፡፡ በሌላ መልኩ መድረክ የሰላማዊ ሰልፉን ዉጤት ተከትሎ መንግስት የሚሰጋባቸውን ችግሮች እንዳይከሰቱ ኃላፊነት በተሞላበት መልኩ ለማድርግ ከመንግስት ጋር ስምምንት ላይ ሳይደርስ እንዳልቀረ የሚያመላክቱ ነገሮች አሉ፡፡ በአቋም እየተለሳለሰ መምጣቱና ለሰልፉ ኃላፊነቱን ከመንግሰት ጋር መጋራቱ ሰልፉን ስኬታማ ለማድረግ ሳይግዘው እንዳልቀረ መገንዘብ ይቻላል፡፡ በ2002 ምርጫ ከኢህአዴግ ጋር […]