“ካላገዝከን ወዮልኽ!” ብሎ ትግል የለም

የፖለቲካ እንቅስቃሴ፣ ሰላማዊም የትጥቅም፣ በባህሪው ትብብርን ይጠይቃል። ሕብረተሰብ በማሳትፍ የሚደረግ የትብብር ሥራ ነውና። የኢትዮጵያ ገዥ ጥምር ድርጅት አንድ አካል የኾነው ህወሓት የፈር ቀዳጅነት ሚናውን ወስዶ የዛሬ አርባ ዓመት በትግራይ በረኻዎች የትጥቅ ትግል ጀምሮ በሚያካሂድበት ጊዜ፣ “ተወዲቡ ብጽንዓት ዝተቓለሰ ይዕወት” (ሲተረጎም፣ ተደራጅቶ በጽናት የታገለ ለድል ይበቃል) የሚል መፎክር ከአነገባቸው መፎክሮች አንዱ ነበር። በነገራችን ላይ የህዝብ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥም ኢህአዴግ እንደ መንግስት ሀገር ሲመራ የተከተለው ህዝብን አደራጅቶ እና አስትፎ የመስራት ባህልም ከዚኽ መፎክር የተወረሰ ሳይኾን አይቀርም። ለዚህም ነው ኢህአዴግ ነጥሮ በመውጣት በትጥቅ ትግሉም ሀገር በመምራቱም ወቅት ውጤታማ ሊኾን የበቃው። አሁን በፖለቲካው ተደራጅተው ሳይደራጁም እየተንቀሳቀሱ ያሉ የተቃውሞ፣ ሕጋዊ የኾኑትም ያልኾኑትም በዋናነት የዚኽ የተባብሮ መስራት ድክመት ስላለባቸው ነው ለውጤት ያልበቁት። ሲጣመሩ፣ ሲቀናጁም ኾነ ሲያብሩ፣ የአብሮ መስራት ምክንያታቸው የመላው ህዝብ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ በፖሊሲ፣ ስትራቴጂ እና ፖለቲካዊ ፕሮግራም ነጥሮ የወጣ ፖለቲካዊ አቋም ይዘው መስዋእት ለመክፈል ተዘጋጅተው ሳይኾን በጥላቻ እና የስልጣን ጥም ብቻ መሰረት አድርገው ነው ወደ አንድ የሚሰባሰቡት። በዚኽ አካሔድ ደግሞ ጠብ የሚለ ውጤት አላገኙም። በተለይ ለመስዋዕትነቱ የሚመርጡት ሌላ አካል እንዲኾንላቸው ይፈልጋሉ። እነሱ በአቋራጭ ስልጣን ላይ ለመፈናጠጥ እንዲያስችላቸው። ከዚኽ አንጻር የሀገራችን ተቃዋሚዎች ትጥቅ ትግል አውጀው በሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩት እና በስመ አክቲቪዝም የሚከትሏቸው (ሁለቱንም መንገድ የሚያጣቅሱ ቡድኖች) እንዲኹም በሰላማዊ ሕጋዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱት በተደጋጋሚ የመተባበር እና ለህዝብ መስዋዕት የመኾን መሰረታዊ ባህሪ ስለሚጎድላቸው እና የስልጣን […]