በምርጫ ዋዜማ – ከ“ተንቤን” እስከ ”ዓዲሓ”

ጽዮን ግርማ – ከተንቤን

በአገሪቱ ቀደም ሲል የተከናወኑት ሦስት ምርጫዎች፤ የትግራይ ህዝብ ከህወሓት ፓርቲ ሌላ እንዲመርጥ ዕድል ሳይሰጡት አልፈዋል። ህወሓት በትግራይ ብቻውን ይወዳደራል፤ ብቻውን ያሸንፋል። የዘንድሮ ምርጫ ግን ይህን ልማድ ገፎ የጣለው ይመስላል፤ ዐረና መድረክ እና አንድነት መድረክ ዕጩዎቻቸውን ወደ ትግራይ ልከዋል።