አንዳንድ ሃሳቦች ስለ ውሃ እና መብራት መጥፋት – ሄኖክ የሺጥላ

ሄኖክ የሺጥላ

ያው እንደምታውቁት ኢትዮጵያ ግድብ እንጂ ውሃ የለም ። ሿ የሚል የውሃ ድምጽ ከጠፋ ቆየ ፣ አረ ተውት !

ድሮ ድሮ ሸራተን ርችት ሲተኮስ ነበር ሰው ጣራ ላይ ወጥቶ የሚያየው አሁን አሁን በቃ ድንገት አንድ ቡዋንቡዋ ለባቡር መንገድ ሲወጣ በስህተት ከፈነዳ በቃ ህዝቡ ከቦ ” ውሃ መጣ ውሃ መጣ ” ነው ። ውሃ ብርቅ የሆነባት ሀገር ሆናለች ። እደውም ከውሃ ዝናብ የመጣበት ቀን ይበልጣል።

በነገራችን ላይ አንድ በጣም ጥቁር ጉዋደኛ አለኝ እና ይሄ ወዳጄ በሚኖርበት አካባቢ ውሃ በተከታታይ ለ አምስት ቀን ጠፍቶ ነበር እናም እስኪ ምነው ይሄ ወዳጄ ጠፋ ብዬ ልጠይቀው ቤቱ ሄድኩኝ ፣ እናላችሁ ሀገር ሰላም ነው ብዬ በሩን አንኩዋኩቼ ስገባ ይሄ በጣም ጥቁር ወዳጄ አይኑ ላይ የተለደፈው አይን አር ፣ አረ ተውት ( አንተ ምነው አትታጠበውም እንዴ ? ) ስለው ፣ “ምን ባክህ ውሃ ከሄደ እኮ ሳምንት አለፈው” አለኝ ። እኔማ በቃ የሜዳ አህያ መስለከኝ አልፌህ ሄጄ ነበር አልኩት ። እንደውም ያ አልብቃ ብሎት “እስኪ ና እንውጣ እና ቁርስ እንብላ ” አይለኝም መሰላችሁ ?! ” ከማ ከኔ ጋ ? በል ዞር በል ደሞ አንተን ሊያድኑ ሲሉ ተሳስተው እኔን ዷ ! አረ አልሄድም ። ደሞ እሱስ ይቅር ቅርስ በማስኮብለል ቢከሱኝስ ? ለማንኛውም ውሃ እስኪመጣ ወይ ከቤት አትውጣ ወይ ካገር ውጣ ! ወይ ቆጥ ላይ ውጣ ! ወይ አይንህን አውጣ ! አልኩት
ለነገሩ ውሃ አልኩ እንጂ መብራቱም ያው ነው ፣ እኛ ሰፈር ጋሼ መብራቱ ብቻ ነው ያልሄዱት ( እሳቸውም አንድ ቀን በ አንቀጽ 39 እንደሚሄዱ ይገመታል )። እንጂ መብራት የተባለ ዘር ማነዘሯ ተነቃቅላ ነው የሄደችው ። እንደውም የሰፈራችን ሴቶች ” ባክሽ ዛሬ አይመጣም አስጭበት !” እያሉ የ ዔሌትሪክ ገመዱን ልብስ ማድረቂያ አድርገውታል ። መብራት ገንዘብ ተቀባዩ እንጂ መብራቱ መምጣት ካቆመ እኮ ቆየ።

ድሮ ድሮ ሰው ተስፋ ሲቆርጥ ” ሄጄ ዔሌትሪክ ነው የምጨብጠው!!! ” ይል ነበር ። አሁን አሁን እንደዚያ ብትል ” ሂድ ጨብጠው ፣ እንደውም አትልቀቀው መብራት ሲመጣ እንድናውቅ !” ነው የሚሉህ ። አይ መብራት ፣ ያፈር መብራት !

የሚገርመው ግን ሰው መብራት ሲሄድ ሳይሆን ሲመጣ ነው የሚጮኸው ! እንዴ ? ምንድን ነው ነገሩ ? ስንጣ ነው ወይስ ስናገኝ መጮህ ያለብን ? ስንፍጉን ወይስ ሲለግሱን ? ወይ እኛ ፣ እንቢ ስንባል ነው ሲፈቅዱልን መጮክ ያለብን ?

ለማንኛውም መብራትን ወስዶ ቻይናን ያመጣ ፣ ውሃን ወስዶ ግድብን ያመጣ አምላክ ይኑር !

ለነገሩ መብራት አልን እንጂ ኢትዮጵያ ምን ያልሄደ ነገር አለ ። እንደውም አንድ አባት ጫት እየቃመ ያስቸገረ ልጃቸውን ” አንተ ልጅ ሉሲ እንኩዋ ዞር ዞር ብላ መጣች። አክሱምም የፓስታ ሽታ ደብሮት ይኸው አሁን ከበሮ ያዳምጣል አንተ ግን መቼ ነው እንደ ሰው መነቃነቅ የምትጀምረው አሉት ። ነገርን ነገር ያነሳዋል እንዲሉ ፣ ዔርትራዊያኖች ከኢትዮጵያ የተገነጠሉት በሲና በርሃ በኩል እስራዔል ለመግባት ነበር እንዴ ? እኛ እኮ ቢነግሩን ፈላሻ ናቸው ብለን በ አውሮፕላን እንልካቸው ነበር ። በእውነት ተሳስተዋል ። ደሞ ሰሞኑን ነው አሉ ” በ አማሪካ ያሚገኘው የኢሳያስ አፈወርቄ ቡድን ለ ጋሼ ኢሳያስ ሶስት ምርጥ ጫማ ገዝቶ ልኮለት ሶስቱም ልኩ በመሆኑ ጋሼ ኢሳያስ ተገርሞ ፣ ” እናንተ እንዴት ቁጥሬን አውቃችሁት? ” ሲላቸው ምን ቢሉት ጥሩ ነው ” 23 ዓመት ረግጠህ ገዝተከን ያንተ የጫማ ቁጥር ይጥፋን ወይ ? ። ወይ መዓልትይ !!! አለ ወያኔ !

እኔ እምለው ሰሞኑን ሃይለማርያም ደሳለኝ መንጃ ፍቃድ ሊያወጡ ሄደው ቪዥን ቴስት ወደቁ አሉ ፣ እና ምነው ሲባሉ ” አይኔን የመለስን ራእይ ለማየት ስለምጠቀምበት ነው !” አይገርምም ?

እስኪ ቸር ይግጠመን !