ፖለቲካና ብልግና ሲቀላቀል
በዉጭ ሀገር በሚኖሩት ኢትዮጵያዊያን መካከል የሚታየዉ ፖለቲካ ነክ አመለካከት በየጊዘዉ እየሰፋና መልኩን እየቀየረ መጥቶዋል ቢባል ማጋነን አይመስለኝም:: ከጥቂት አመታት በፊት በውጭ ሃገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የተቃዉሞ ሰላማዊ ሰልፍ ወጡ የተባለ እንደሆነ የኦነግ ደጋፊዎች ጩሄት ግፋ ቢል ደግሞ የሃይማኖት ቡድን ደጋፊዎች መሆናቸዉን መገመት ቀላል ነበር:: ከምርጫ 97 ቦሓላ ያለዉ ታሪክ ግን ከዚህ በእጅጉ የሚለይ ሆኖ እናገኛለን:: በተለይ አብዛኛዉ ኢትዮጵያዊ መቼም የማይረሳዉና ያለምን ማህበረሰብ ያስደነገጠዉ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የተወሰደዉ አረመነያዊ የአቶ መለስ ወታደራዊ እርምጃ በነዚህ ኢትዮጵያዊያን መካከል እየሰፋ ለመጣዉ የፖለቲካ አመለካከት በምክንያትነት ይጠቀሳል:: ያንን ተከትሎ የቅንጅት መሪዎችና ደጋፊዎች መታሰር; የወይዘሪት ብርቱካን ድጋሚ መታሰር; በምርጫ 2002 የታየዉ ዓይን ያወጣ የኢሕአደግ ማጭበርበርና ሌሎቹ አብይ ምክንያቶች የጎራዎቹን ልዩነት በየጊዘዉ እያሰፉት ሄደዋል:: ልዩነቶቹ አሁን የደረሱበት ደረጃ ግን በኔ ዓይነቱ ፖለቲካ ብዙም ያልገባዉ ሰዉ አመለካከት ሲቃኝ እጅግ አስገራሚ ይመስላል:: የሚያስገርመዉ የልዩነቱ እየከረረ መሄድ ብቻ ሳይሆን በቡድኖቹ መካከል የሚታየዉ የከረረ ልዩነት ከድህረ-ገጽና ከጋዘጣ ጦርነት አልፎ ወደ አካላዊ ጦርነት መቀየሩ ነዉ:: ለዚህም እንደ አብነት የሚጠቀሱት በኒዉዮርክ የአቶ መለስን መጋበዝ የሚደግፉና የሚቃወሙት መካከል የተፈጠረዉ ግጭት, ወይዘሮ አስቴር ማሞን በሲያትል ያጋጠማቸዉና ስብሰባቸዉን ያስትጎዋጎለባቸዉ እንድሑም ከቀናት በፊት በዳላስ አንድን የኢሕአደግ ባለስልጣን በሉት ካድረ ያጋጠማቸዉን መጥቀስ ይቻላል::
አነሳሰ ስለልዩነቶቹና ስለመፍትሄዎቹ መዳሰስ አይድለም:: እሱን ለነፕሮፌሰር አልማሪያም, ለጀዋር ሲራጅና ለመሰሎቹ መተዉ መረጥኩ:: ይልቅስ ትኩረተን የሳበቺዉን ነገር ላጫዉታችዉና ላብቃ:: አንድ ኢትዮጵያዊ ድረ-ገጽ ላይ በተለጠፈው ቭዲዮ ላይ እንዳየሁት እላይ በጠቀስኩት ‘የዳላስ ጦርነት’ ላይ አንድ ኢትዮጵያዊ በወያነ ወታደሮች በገፍ ስለተጨፈጨፉ ኢትዮጵያዊያን ሲያነሳ አንዱ የወያነ አባል ይሁን ደጋፊ ቱግ ብሎ አከከ ዘራፍ ማለቱ ስገርመኝ ሰዉየዉ ጭራሽ ዘሎ በመነሳት በጫት ተራ የሚሰማዉን የስድብ ናዳ በፖለቲካ መድረክ ተብይው ላይ ማዉረደን ቅጠለ:: ከዛም አልፎ ጭራሽ ሊማታ ሲታገል አይቼ እግዚኦ! ወይ ኢትዮጵያ ሀገረ ምን ይሻልሻል? ብዬ ብቻየን መተከዝ ጀመርኩ:: አንድ አፍታም ኤረ ለመሆኑ የዚህ ዓይነት ስዉየ አዲሳባ ባሉት የኢሕአደግ ባለስልጣናት መሃል ስንት ይሆናሉ ብየም አሰብኩ:: አንደበትን ሳይገዙ ሃገር መግዛት:: ለመሆኑ ፖለቲካ ማለት ለኢሕአደግ ስነ-ምግባር የለሌው የብልግና ዉድድር መሆኑን ማን አስተማረዉ? ይሄ ሰዉየስ ወያነ በግፍ የገደላቸዉ ሰዎች ጉዳይ ሲነሳ ምን አንገሸገሸዉ? ‘የወጋ ቢረሳ,..’ የተባለዉን ተረት አልሰማም ልበል? ወይስ የሁለም ሰዉ ጭንቅላት እንደሱ በሆድ መሸፈን አለበት? ለማንኛዉም እያወቃችሁ ይህንን ጨዋ ሕዝብ የሚትበድሉ; ለጊዘያዊ ጥቅም ስትሉ ዘጎችን እንደጠላት የሚትፈርጁ; ነገን ዘንግታችሁ በዛረ ስሌት ብቻ የሚትንቀሳቀሱና ከሁሉም በላይ ደግሞ የዘጎችን እንባ ችላ ብላችሁ ለሆዳችዉ ብቻ የሚትኖሩ ሰዎች ይህቺ ሃገር ደሃ ብትሆንም አምላኩዋ ታጋሽ ግን ቀናተኛ አምላክ ስለሆነ በግዘ የበደላችሁትን ይህን ጨዋ ሕዝብ እርስ ከራሱ ጋር ብታስታርቁና ራሳችዉም ከራሳችሁ ጋር ብትታረቁ መልካም ነው:: አበቃሁ::
ዓለሙ ኢተፋ
ከለንደን