የህወሓት ሦስቱ ጉልቾች ስሪትና ተግባራቸው፡፡ ከላገሬ ኢትዮጵያ

የጉልቾቹ ስም ብአዴን፣ኦህዴድ፣ደህዴን ሲባሉ የተሰሩትም ዴሞክራሴ ከተባለ ዘረመል(ሴል) ሆኖ ይህ ሴል ያለማችን ገራሚው የጉልቾች ሴል ተብሎ እንዲመዘገብ እራሱን ነፃ አውጭ ብሎ የሰየመው ህወሓት ባለም ቅርስነት እንዲመዘገብ አድርጉዋል፡፡

ይህ ሴል በውስጡ ሂዎት የሌለው አርቴፊሻል የህወሓት የላባራቶሪ መመራመሪያ ሲሆን እስካሁንም ወደር ያልተገኘለት ሂዎት አልባ ተንቀሳቃሽ ቁስ ግን የዎያኔ መጠቀሚያ ሆኖ ያገለግላል፡፡

አስገራሚው ነገር ህወሓት የሚባለው በድን የዴሞክራሴ ሴል ሰራሽ አካል የዴሞክራሴ ፅንሰ ሀሳብ የሌለው እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ብሎ የሰየመ ሆኖ አላማውም የትግራይን ህዝብ እና ህዝብ ብቻ ነፃ ለማውጣት የተቋቋመ ጠባብና ዘረኛ የፖለቲካ አጀንዳ ያነገበ መሆኑ ነው፡፡

ሌላው ገራሚ የሚያደርገው ነገር እራሱን ህወሓትን ጨምሮ ሌሎች ኦህዴድ፣ደህዴን በድን የዲሞክራሴ ሴል ውስጣቸው እንዳለ ተደርገው የተሰሩት ቁሶች ህዝብ የሚል ሌላ የሚያምታታ ማጭበርበሪያ ታቤላ የተለጠፈባቸው ሲሆን ብአዴን የሚለው ጉልቻ ግን ከህዝብ ይልቅ ብሄር የሚል መታወቂያ ተሰጥቶታል ምክንያቱም ይህ ስም ለህወሓት የፖለቲካ መሳሪያ በቀጥታ ላገልግሎት እንዲጠቅም ተፈልጎ ነው፡፡
እዚህ ጋር መጤን የሚገባው ነገር ብሄር በሚለው ስም ብሄርብሄረሰቦች የሚለውን ሌላ የፖለቲካ ትርፋ ለማምጣትና የሰደቅ አላማውን የቀድሞ ልዕልናውን ለማሳጣትና የምሐለኛውን ሴጣናዊ ምናምንቴ በብሄር ብሄረሰብ ስም ለመለጠፍ ተፈልጎ የተሰራ አገር የማፍረስ ደባ ነው፡፡

አሁን ህወሓት በዚህ መልኩ ጉልቻዎቹን ከሰራ በሗላ ሁሉንም አንድ ለማድረግ የተጠቀመበት ዘዴ ጉልቾቹ ከተሰሩበት በድን የዴሞክራሴ ሴል በቀጥታ ሴሉን በመውሰድ ኢህአዴግ ብሎ በመሰየም ዋና ህዝብን ለማወናበድ ወደሚጠቀምበት አዛኝ ቅቤ አንጉዋች እንደሚባለዉ የጭቃ እሾኩን በኢትዮጵያ ህዝብ ውስጥ ተከለ፡፡

አሁን የሚቀረዉ ቁጭ ብሎ በነዚህ ከንቱ ያትራፊነት የሴራ መረብ በመጠቀም ምሁር ነን የሚሉትን ሁሉ በማታለልና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ይፈቀዳል፣መናገር ይቻላል፣መፅፍ ይቻላል እናም ሌሎች ኘሮፖጋንዳዎችን በመናገርና ህገመንግስት እያለው በሚጠራው ምናምንቴው ለይ የፃፈዉን በማየት ህብረተሰቡ እውነት መስሎት ተሸወደ ምሁሩም ተግባራዊ ለማድረግ ሞከረ ግን እንደማይቻል ሲያውቅ የታሰረውም ታስሮ ሞት የተፈረደበትም ተገደለና ጥቂት የማይባለው ወገኔ ሲሰደድ አብዛኛው ህብረተሰብ በሲቃይ መዓበል ውስጥ መፍተሄ አልባ የፅር ድምፅ እያሰማ በሐገሩ ባይተዋርና የበይ ተመልካች ሆኖ ተቀምጡዋል፡፡

ሶስቱ ጉልቾች የህወሓት የጀራ መጋገሪያ ምጣድ ለማስቀመጭያነት በቀጥታ የዋሉ ሲሆን አንዳንድ ግዜም ወጥ ለመስሪያ የሚጠቅም ድስት መጣጃዎች ሆነው እናያቸዋለን እዚህ ጋር ግን ሌላ ማስተዋል የሚጠበቅባችሁ ነገር የጉልቻዎቹ ትክክለኛ በድንነት የምትለዩት ምንም እሳት ቢነድባቸው ሚሊዮን እንጀራ ቢጋገርባቸው ቅንጣት የማይሰማቸው ስሜት አልባ እቃዎች መሆናቸዉ ነው፡፡

የሰወስቱ ጉልቾች አባላቶችና ደጋፊዎች ሆይ እባካችሁ ፈጣሪ ነፍስ ከዘራባችሁ ይህንን አንብቡትና የህወሓትን ስውር አደንዳ ከስር መሰረቱ ለመገርሰስ ሞክሩ ቢያንስ ለልጅ ልጆቻችሁ ታሪክ ነውና ንቁ፡፡ይሄንን ለማድረግም አይመሽባችሁም እስኪ ግማሾቻችሁ እንኩዋን በቃን ብላችሁ የዚህ አይነቱን የርግማን እንጀራ ከመብላት ተቆጠቡ ምክንያቱም አሁን የምትበሉት የህዝብ ስጋ ሲሆን የምጠጡትም የወገናችሁ እንባና ደም ነዉና ትውልድ ይዳን ትላንት የገደላችሁትና ያስገደላችሁት የግፍ ፅዋ ይብቃ እላችሗለሁ፡፡

ከላገሬ ኢትዮጵያ
03/03/2007
Image