ሥራአጥ ፈላስያንና የአውሮፓ ሕብረት ፍ/ቤት

የአውሮፓ ፍርድ ቤት ትናንት ሉክስምቡርግ ላይ ባስቻለው ችሎት የጀርመን መንግሥት ፣ ኤልሳቤት ዳኖቭ ለምትባለው ሩሜኔያዊት የስራ አጥ ድጎማ መከልከሉ አግባብነት ያለውና በሕግም የተመሠረተ ነው ሲል ውሳኔ አሳለፈ።