ኢትዮጵያ ‘የስቶክ ገበያን’ ከ50 ዓመታት በኋላ ድጋሚ መክፈት ለምን አስፈለጋት?
ኢትዮጵያ ከ50 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የስቶክ ገበያን ክፍት አድርጋለች። ኢትዮ ቴሌኮም ኢኤስክስን በመቀላቀል የመጀመሪያው የልማት ድርጅት ይሆናል። ሌሎችም ድርጅቶች ይህንን የግብይት መድረክ እንደሚቀላቀሉ ተነግሯል። የኢኤስኤክስ መከፈት ለኢትዮጵያውያን ምን ይዞ ይመጣል? ችግር ላይ ያለውን የአገሪቱን ምጣኔ ሀብት እንዴት ሊደግፍ ይችላል?