የአንድነት ለዲሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ የነበረው አቶ ደረጀ ክበበው ከዚህ ዓለም ተለየ

የምስራቅ ሸዋ ዞን አዳማ የአንድነት ለዲሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ የነበረው አቶ ደረጀ ክበበው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡ አቶ ደረጀ በጠና ታሞ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ትላንት ጠዋት በአዳማ ከተማ ቀበሌ 07 በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ያረፈ ሲሆን የቀብር ስነስርዓቱ በትላንትናው ዕለት ከቀኑ በ 7፡00 ሰዓት አዳማ በሚገኘው መድኃኒአለም ቤ/ክርስቲያን ተፈጽሟል፡፡ ፓርቲው በአቶ ደረጀ ክበበው ሞት የተሰማውን ሀዘን ገልፆ ለቤተሰቡና ለትግል አጋሮቹ መጽናናትን ተመኝቷል፡፡10305327_722884921129778_996670768286398834_n