በሲድኒ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ለፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ልዩ ክብር ሰጡ!
ከአቢይ አፈወርቅ
– ደማቅ ውይይትም አድርገዋል።
ዕውቁ የሰብዓዊ መብት ተሟጋችና ምሁር ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም ባለፈው እሁድ ኦክቶበር 26 ቀን በሲድኒ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ጋር ደማቅ ውይይት ያደረጉ ሲሆን ልዩ የምስጋና ስጦታም ተበርክቶላቸዋል። በዕለቱ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያዊያን ተገኝተው አዳራሹ በመሙላቱ የተወሰኑ ታዳሚዎች ከፊትና ከኋላ ባሉ በረንዳዎች ላይ ተደርድረው ፕሮግራሙን ለመከታተል መገደዳቸው ይህ ሪፖርተር ተመልክቷል።