የሚሊዮኖች ንቅናቄ – መደመጥ ያለበት የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ገጽታ የሚያስረዳ ቅንብር
ገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አሥራ አንደ በመቶ በላይ፣ ለበርካታ አመታት እንዳደገ ይናገራል። በአገሪቷ በተለይም በአዲስ አበባ ግንባታዎች ይታያሉ። መንገዶች ይሰራሉ። ነገር ግን ግንባታዎቹ በአብዛኛው ከዉጭ በልምና በመጣ ገንዘብ የተሰሩ እንደመሆናቸው የኢትዮጵይን ምርታማነትና እድገት አመልካች አይደለም። የብር የመግዛት አቅም ከማሽቆልቆሉ የተነሳ፣ በቀን አንድ ጊዜ ብቻ የሚመገበው ሕዝብ ቁጥር በጣም እየጨመረ መጥቷል።
የኢሕአዴግ ባለሥልጣናት ተመዝግቧል የሚሉት የኢኮኖሚ እድገት በርግጥ እድገት ነው ወይ ? ከሆነስ ስለምን ህዝቡ የእድገቱ ተካፋይ ሊሆን አልቻለም ? ለሚሉት ለመሳሰሉት ጥያቄዎች በጥናትና በመረጃ ላይ ያተኮረ መልስ ለማግኘት፣ በቃሌ የፓልቶክ ክፍል የቀረበ፣ በአንድነት ደጋፊዎች የተቀናበረና የተዘጋጀ፣ ገለጻ ያዳምጡ።