አቡነ ማትያስ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለን አካል አክራሪና አሸባሪ ካሉ በውግዘት እንደሚለዩ ቅዱስ ሲኖዶሱ በጥብቅ አስጠነቀቃቸው! የዕለቱ የምልአተ ጉባኤው ውሎ በድንገት ተቋረጠ
- ያደረውን የሕገ ቤተ ክርስቲያን አጀንዳ በፈቃዳቸው ትተው ሌላ ርእሰ ጉዳይ አንሥተዋል
- የተቃወሟቸውን አባቶች በአሳፋሪ ንግግሮች በመዝለፍ ለማሸማቀቅ ሙከራ አድርገዋል
- የሕገ ቤተ ክርስቲያኑ አጀንዳ ቀጣይነት በድምፅ ሊወሰንበት እንደሚችል ተመልክቷል
- እንደ ሕጉ ስብሰባውን በአግባቡ ካልመሩ ምልአተ ጉባኤው ሌላ ሰብሳቢ መርጦ ይቀጥላል
* * *
- ‹‹ተጠሪነትዎ ለቅዱስ ሲኖዶስ ነው፤ በቤተ ክርስቲያን ሕግ ቢመሩ፣ ቅዱስ ሲኖዶሱን ቢያከብሩ ይሻልዎታል፤ ሕግ አይገዛኝም ካሉ ወዳልተፈለገ አቅጣጫ እንሔዳለን፡፡›› /ቅዱስ ሲኖዶሱ/
- በቅ/ሲኖዶስ ከተወሰነው በተፃራሪ ማኅበሩ ለልዩ ጽ/ቤታቸው ሳያሳውቅ አንዳችም መርሐ ግብር እንዳያከናውንና ከስብሰባው መጠናቀቅ በኋላ የሚወስዷቸውን ሕገ ወጥ ርምጃዎች መከላከልን በተመለከተ መመሪያ እንዲሰጥ ብፁዕ ዋና ጸሐፊው እና ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ጠይቀዋል፡፡
- ‹‹ማኅበራት ገንዘባቸውን ወደ ማእከላዊ ካዝና ያስገቡ ይላሉ፤ የማኅበራት ዓላማ ገንዘብ ማሰባሰብ አይደለም፤ ገንዘብ አሰባሳቢ አይደሉም፤ ለተቋቋሙበት ዓላማ ያሰባሰቡትን ገንዘብ ግን እንዴት ሥራ ላይ እንዳዋሉት መቆጣጠር ይገባል፡፡››
- ‹‹ዓላማዎ ማኅበሩን መዝጋት ነው፤ አይደለም? አይዘጋም!››
/የምልአተ ጉባኤው አባላት/
