የበርቱዎ ጊዜ (ዘመን)

የተማረ አይደለም ሰው የሚያስተምረው ?
ግራ ቀኙን አይቶስ ምሬአለሁ የሚለው ?
ህግን ስለተማርሽ ዛሬ አስተማርሻቸው
የዘሩትን ማጨድ ይሉሻል ይሄ ነው።
ተመስገን ለእውነትሽ ዛሬ ነፃ ወጣሸ
ተምረሽ መፍረድን እሰዬ ይመስከርልሽ
ብርቱነሽ ብርቱካን ለህዝብሽ ዘብ የቆምሽ
ለወንድምሽ ስዬ እውነት ስለፈረድሽ
እህት ወንድሞቹ ንግስት ነሽ አልንሽ።
መከራው ፈተናው ማምለጫው ቀጠነ
የ “ኢትዮጵያ” ጀግኖች ዘራቸው መከነ
ብሎ እኮ በማሰብ ሕዝብ እንዳላዘነ
ብርቱካን ባንቺ አንደጉም ተነነ
ስጋታችን ጠፍቶ ጀግንነት ጀገነ።
ከስር ስለወጣሽ “አንድነት” አደረግሽ
ጥጡን ከጥፍጥሬ ለይተሽ ጐልጉለሽ
ፍልቅቁን አባዝተሽ በደጋን በተንሽ
ነድፈሽ በእንዝርቱ ላይ
ጠምጥመሽ ሰብስበሽ
ከላይ ወደ ታች ያን ፈትል አዋቅረሽ
አረንጛዴ፡ ቢጫ፡ ቀይ ፡ቀለሙን አቅልመሽ
ፈተለሽ ብርቱካን ፈተለሽ በእንዝርትሽ
ሸማኔውም ሕዝብሽ ያአላማ አጋርሽ
“አንድነት” ያለው ውል
እናት ሀገርሽ
እንኳንስ ደስ ያለሽ
ህዝብሽን አኮራሽ።

– ራሄል ጌታቸው