የኤርትራዉያን ስደት ዘጋቢ ፊልም

ባለፈዉ ዓመት540 ሰዉ የጫነት አንዲት ጀልባ በሜዲትራኒያን ባህር ዉስጥ ስትሰጥም ወደአራት መቶ የሚሆኑት ህይወታቸዉ ማለፉ ይታወሳል። ሁኔታዉን አሳፋሪ የታሪክ ጥላሸት ሲሉ የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ተችተዉታል። የእሳቸዉን አባባልም አብዛኞች ደግመዉታል።