ኢትዮጵያ እና የኢንተርኔት አገልግሎት

ኢንተርኔት ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ በዋለባቸው ያለፉት ሁለት ዐሠርተ- ዓመታት ውስጥ በዓለም ሕዝብ ፤ መንግሥታትና ተቋማት የርስ በርስ ግንኙነት ላይ ጉልህ ተጽዕኖ ፈጥሯል። ቴክኖሎጂው አዳዲስ ግኝቶችንና ፈጠራዎችን በማበረታታት ሃገራት ዓመታዊ የምርት መጠናቸውን (GDP) እንዲያሳድጉ በር ከፍቷል።