የ«አይ ኤስ» የጭካኔ ተግባር እና የብሪታንያ ውግዘት
ራሱን «አይ ኤስ» ወይም እስላማዊ መንግሥት ብሎ የሚጠራው ፅንፈኛ ቡድን ከአንድ ዓመት በፊት በሶርያ አግቶት የነበረውን የ47 ዓመት እንግሊዛዊ አለን ሄኒንግን አንገት ቀልቶ መግደሉን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን በጥብቅ በማውገዝ የብሪታንያ መንግሥት በቡድኑ እና በሀገሪቱ አሉ በሚባሉ የቡድኑ ደጋፊዎች ላይ የማያዳግም ርምጃ እንዲወስዱ ጠይቀዋል።