በጋምቤላ ክልል የተፈናቀሉ እና ከዘር ማጥፋቱ የተረፉ አማሮች ወደ መኢአድ ቢሮ መጡ! አቶ ተስፋሁን አለምነህ

በፋሽሽቱ ወያኔ ከጋምቤላ ክልል በግፍ የተፈናቀሉ እና ከዘር ማጥፋት ወንጀል የተረፉት አማሮች ወደ መኢአድ ጽ/ቤት መጥተዋል፡፡

በጋምቤላ ክልል ሜጢ ከተማ ጎሽኔ ቀበሌ አቶ በለጠ ጌታቸው ጎጃም ቢቸና አካባቢ የመጡ የግራ እጃቸውን በከፍተኛ ሁኔታ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

gambella1

gambella2

gambella3
በዚሁ ቀበሌ ከወሎ መካነሰላም ቦረና አካባቢ የመጡ አቶ ገበየሁ ኮስትር በጀርባቸው በኩል በከፍተኛ ሁኔታ በጥይት ከተመቱ በኋላ ጥይቱ በሰውነታቸው ውስጥ ይገኛል፡፡ በአካባቢው በተደረገላቸው ህክምና ጥይቱን ማውጣት ስላልተቻለ በከፋ ስቃይ ውስጥ ይገኛሉ፡፡

በተጨማሪም ቤተሰቦቻቸው ይሙቱ ይዳኑ ምንም አይነት መረጃ ባለማግኘታቸው በጭንቀት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ወ/ሮ ጀምበሬ ኮስትር፣ወ/ሮ ሳዓዳ ተፈራ፣ ወ/ሮ ኮከቤ ኮስትር ከእነ ህፃን ልጆቻቸው በባሰ ችግር ውስጥ ሆነው ወደ መኢአድ ጽ/ቤት በመምጣት በሰቀቀን ችግራቸውን ተናግረዋል፡፡

ተፈናቃዮችና ከዘር ማጥፋት የተረፉት፤ እኛስ ከእነ ችግሩም ቢሆን የተወሰነ ድጋፍ አግኝተናል፡፡ ከዚያው የቀሩት ወንድሞቻችን ጉዳይ በእጅጉ ያሳስበናል ካሉ በኋላ ለእኛም ሆነ ለወንድሞቻችን የኢትዮጵያ ህዝብ በአሰቸኳይ እንዲደርስልን ሲሉ ተማጽነዋል፡፡

መከፋፈልና የተናጥል ጉዞ የሚጠቅመው አምባገነኖችን ብቻ ነው !