ከመብረርዎ በፊት ራጅ ሊነሱ ነው

Photo:MIKE SIEGEL

በሲያትል የሚገኘው ሲታክ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መንገደኞችን የሚፈትሽ የኤክስ ሬይ ማሽን መትከሉ ተዘግቧል። ፍተሻው ከመደረጉ በፊት መንገደኛው በኪሱ የሚገኝ ማናቸውም ከብረትም ሆነ ከፕላስቲክ የተሠራ ዕቃ በሙሉ ማውጣት ይጠበቅበታል። ለጥቆ መንገደኛው ዕጅ ወደላይ እንደተባለ ወንጀለኛ ሁለት ዕጆቹን ወደሰማይ ዘርግቶ መሳሪያው ራጅ ያነሳዋል።
ይህ ለተጓዦች ደህንነት ጠቀሜታው አሌ ባይባልም 3 ዓቢይ ችግሮች አሉት ተብሎ ይገመታል፤

የግለሰቡን ነጻነት ይጋፋል፡ የተነሳው ስክሪን ወድያውኑ እንዲጠፋ ይደረጋል ቢባሉም በፍተሻ አባላት መታየቱ አይቀርም

በኪስ የሚገኙ ቁሳቁሶች ማለትም እንደ ሰዓት፣ ቀበቶና ማበጠሪያ በሙሉ እስከሚወገዱ ጊዜ ስለሚወስድ የሚያሰላች ወረፋ ያስከትላል

ራጅ እንደሚታወቀው የጤና ችግር ሊያስከትል ይችላል። መጠርጠር አይከፋም።

ከላይ የተጠቀሰው የራጅ መፈተሻ መሣሪያ ከጤናና መብት አኳያ ተቃውሞ ካልገጠመው በስተቀር ወደ ሁለት ሺህ በሚጠጉ የዩናይተድ ስቴትስ አውሮፕላን ማረፊያዎች ሊገጠም እንደሚችል ይነገራል። በዓመታት አንድ ጊዜ ለሚጓዝ የራጅ መሣሪያ መተከል ባያስጨንቀውም ብዙ በረራ ለሚያደርጉ ሰዎች ግን በጎ ዜና አይደለም።

ምንጭ፡ ሲያትል ታይምስ

5/5/10