ኢትዮ-ቻናል እና የፊት ገጹ
“ኢትዮ-ቻናል” ሲቆላመጥ “ቻናል” ይባላል፡፡ በአገር ቤት በሳምንት ሁለት ጊዜ ለመታተም የታደለ ጋዜጣ ነው፡፡ ባለፈው ሳምንት የረቡዕ ዕትሙ “የዲያስፖራ ፖለቲካን” ክፉኛ የሚተቹ ጽሑፎችን እንጂ አንድም የተለመደ የጋዜጣ ዜና ይዞ አልወጣም፡፡ በፊት ገጹ የመጀመርያ ርእሰ-ጉዳይ ያደረገው “ኢትዮጵያን ሪቪው” የተሰኘውን ተነባቢ ድረ-ገጽን ነው፡፡ የድረ-ገጽን ባለቤት አቶ ኤልያስ ክፍሌ ከኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያሳ አፈወርቂ ጋራ የተነሱትን ባለቀለም ፎቶ አትሞታል፡፡ የሚከተለውን ርዕስ ሰጥቶታል-“ጽንፈኛ ዲያስፖራዎች በሰሜን አሜሪካ እግር ኳስ ላይ የዘቀጠ ፖለቲካቸውን ይዘው ገቡ፡፡ የኢሳያስ ቅጥረኛ የኾነው ኢትዮጵያን ሪቪው ሰርጎ ገብቷል፡፡”
ከዚህ ዜና ባሻገር ብርቱካንን፣ ዶ/ር ያዕቆብን እና መኢአድን የሚተቹ የተለያዩ ገጾቹን የሸፈኑ ጽሑፎች ነበሩት፡፡ የቻናል ገጾች ትችት ብቻ አይደለም የያዙት፤ ሙገሳም አለበት፡፡ ለምሳሌ በፊት ገጹ “ማለቂያ የሌለው ደግነት” በሚል ርእስ ቢሊየነሩን ሼሕ አል-አሙዲንን የሚያሞካሽ ረዥም ጽሑፍ ከእነፎቶግራፋቸው አትሟል… [ይቀጥላል]