የማለዳ ወግ… በ2006 ዓ.ም የመጨረሻ ሰዓታት፣ የማይረሱኝ የተጨመቁ ትዝታዎች
ነቢዩ ሲራክ
አዲስ የነበረውና ዛሬ ገና 12 ወር ከ5 ቀኑ “ያረጀ ያፈጀ ” የምንለው 2006 ዓ.ም ለመገባደድ ጥቂት ሰአታት ብቻ ነው የቀሩት። 2006 ዓ.ም በሳውዲ ለምንገኝ ኢትዮጵያውያን ልዩ የማይጠፉ ትዝታዎቸን አስተናግደንበታል።
* ፍጹም የማይረሱኝ ትዝታዎች …
በ2006 ተከስተው የማይረሱኝ የተለያዩ ክስተቶች እና አስደሳችና መራራ ትዝታዎች ብዙ ቢሆኑም የተጨመቁትንና ፍጹም ከአዕምሮየ የማይጠፉት በአዲሱ አመት መግቢያና በአሮጌው አመት መሸኛ የመጨረሻ ሰአታት ላድታውሳቸው ግድ አለኝ …