የጀርመን እና ኢትዮጵያ ትብብር ስምምነት

ኢትዮጵያና ጀርመን የሁለትዮሽ ትብብር ዉል ተፈራረሙ። ትናንት የገንዘብ እና የኤኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ዴታ አቶ አህመድ ሽዴ እና የፌደራል ሪፑብሊክ ጀርመን የኤኮኖሚና ልማት ምክትል ሚኒስትር ቶማስ ዚልበርሆርን ለሁለቱ ሃገራት የተፈራረሙት የትብብር ዉል ከጎርጎሪዮሳዊዉ 2015 እስከ 2018ዓ,ም የሚዘልቅ ነዉ።