ግድያና ሁከት በፈርግሰን

በዩናይትድ ስቴትስዋ የሚዙሪ ግዛትበምትገኘው በፈርግሰን ከተማ አንድ ጥቁር ወጣት በነጭ ፖሊስ ከተገደለ በኋላ የተነሳው ተቃውሞ አሁንም አልቆመም ። ትናንት ማታም ተቃዋሚዎች በፖሊስ ላይ ጥቃት መሰንዘራቸው ተሰምቷል ። ትንናት ማታ ተቃዋሚዎች ውሃና ሽንት የያዙ ፕላስቲኮች ወደ ፖሊስ መወርወራቸውን ፓሊስ አስታውቋል ።