በአምሥት መፅሄቶችና በአንድ ጋዜጣ ላይ ክስ መመሥረቱ

ከመፅሄቶቹ ዋና አዘጋጆች አንዳንዶቹ ለዶቼቬለ በሰጡት አስተያየት ሥራቸውን በህጉ መሠረት እንደሚያከናውኑ ተናግረዋል ። ክሱን በተመለከተም ከህዝብ ጋር በቴሌቪዥን ከመስማታቸው ውጭ እስከ ዛሬ ከቀትር በኋላ ድረስ ምንም ዓይነት መጥሪያ ሆነ ክስ እንዳልደረሳቸው አስታውቀዋል ።