የአፍሪቃ አሜሪካ ጉባኤ

ዛሬ በዋሽንግተን ዲሲ ዩናይትድ ስቴትስ የሚካሄደዉ የአፍሪቃ አሜሪካ ጉባኤ ዩናይትድ ስቴትስ ፈጣን እድገት እያስመዘገበች የምትገኘዉ የአፍሪቃ አህጉር ላይ ያላትን ፍላጎት እንደሚያሳይ ነዉ የተነገረዉ። የጉባኤዉ አዘጋጆች ዓላማዉ የተጠናከረዉ የቻይና አፍሪቃ የንግድ ግንኙነት ያስከተለዉ ነዉ የሚለዉን ጥርጣሬ ወደጎን ነዉ ያደረጉት።