ኢትዮጵያ የሥልክና የኢንተርኔት ችግር

የሐገሪቱን የሥልክና የኢንተርኔት አግልግሎት በብቸኝነት የሚቆጣጠረዉ ኢትዮ-ቴሌኮም በየጊዜዉ ለሚነሱት ወቀሳዎችና ለሚፈጠሩት ችግሮች ምክንያት የሚላቸዉን ቴክኒካዊ ሠበቦች መደርደሩ አልቀረም።ችግሩ ግን የመቃለል እዝማሚያ አልታየበትም።