የግል ሚዲያው “በጸረ ሽብር ህግ” ሊበላ ይሆን?
አቶ ግርማ ሰይፉ
የመንግሰትን ቀጣይ እርምጃ የሚያሳዩ ተከታታይነት ያላቸው በግል ሚዲያዎች ላይ የሚደረጉ ዘመቻው ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ መልክቶች እየታዩ ነው። በቀጣይ ለሚቀርበው ዶክመንተሪ ተጋባዥ አንግዳ ሆኜ ለቆርጦ ቀጥሉ ኢቲቪ ቃለ ምልልስ እንደሰጣቸው ጥያቄዎቹ ደረስውኝ ተመልክቸዋለሁ። የጥያቄዎቹን ዝርዝር እንተወው እና ዓላማው ግን ባለፈው ከቀረበው ዘጋቢ ፊልም የተለየ ነገር የለውም። በነገራችን ላይ ባለፈው የቀረበውም ዘጋቢ ፊልም ላይ እንድሳተፍ ተጠይቄ እንደማይሆን ገልጨላቸው ነበር። ውሳኔዬ ትክክል መሆኑን ዘጋቢ ፊልሙን ካየሁ በኋላ ገብቶኛል።