በአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የሴቶች ጉዳይ የተዘጋጀው ውይይት ከጠዋቱ 3፡30 ጀምሮ ተካሄደ -የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት

በመክፈቻው ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የሴቶች ተሳትፎ በኢትዮጵያ የሴቶች ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ በእጅጉ አሳስቦአችሁ ጊዜያችሁን ሰውታችሁ በዚህ ስብሰባ ላይ በመገኘታችሁ በአንድነት ፓርቲ ስም ከፍተኛ ምስጋና አቀርባለሁ ካሉ በኋላ እንዲሁም የጽሑፍ አቅራቢ ወ/ሮ አልማዝ ሰይፉ ለሴቶች እንቅስቃሴና የእኩልነት ጥያቄ ትምህርት ለመስጠት በመሀከላችን በመገኘቷ በናንተና በፓርቲው ስም ከፍተኛ ምስጋና አቀርብላታለሁ፡፡ ሴቶች በቀን ከ12 – 16 ሰዓት የሚሰሩ በአማካይ የ20 ሚሊዮን ቤተሰብ ማናጀር (ሥራ አስኪያጅ) ሴቶች መሆናቸው ከማንም በበለጠ የሀገሪቱ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ልማት መሰረቶች ሆነው ነገር ግን ውሳኔው የወንዱ መሆኑን እኩልነቱ የጠፋውም ከቤት እስከ አገር አቀፍ መሆኑን ፓርላማው፣ ሚኒስትሮች ም/ቤት፣ የፍትህ አካላቱም የወንድ ቤት ነው ብለዋል፡፡ ሰራተኞቹ ሴቶች የስልጣን ተጠቃሚው ወንድ ከሆነ ይህ ፍትሃዊ አይደለም፡፡ ሴቶች ይህንን የተዛባ የፖለቲካ ስርዓት መለወጥ አለባችሁ ብለዋል፡፡

በመቀጠል የሴቶች ተሳትፎ በኢትዮጵያ ፖለቲካ የነበረ ያለና ሊሆን የሚገባው በሚል ርዕስ በታዋቂዋ ፖለቲከኛ ወ/ሮ አልማዝ ሰይፉ ጽሁፍ የቀረበ ሲሆን እሳቸውም ይህን ርዕስ ወስጄ እዚህ በመቅረቤ የተሰማኝን ደስታ በቅድሚያ እገልፃለሁ ካሉ በኋላ እዚህ የተገኛችሁ ወንድሞቻችን ለዲሞክራሲ ግብአት የፆታ ትግል ብቻውን ምንም ስለማያመጣ ይሄንን ርዕስ አክብራችሁ የዲሞክራሲ አካላቶቻችን እህቶቻችን ናቸውና የነሱን ጉዳት ብቻ ሳይሆን የነሱንም መብት ለማክበር መጥተናል ብላችሁ ስለተገኛችሁ በእጅጉ አመሰግናችኋለሁ ብለዋል፡፡
**ቀጣዩን ክፍል እናቀርባለን**1795611_673674006050870_2513233473303674192_n