የአፍሪካ ነገር-የኢትዮጵያ ነገር
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም
በሃያኛው ምዕተ-ዓመት ላይ የታወቀ የፈረንሳይ ፈላስፋ ነበረ፤ እሱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ በነበረበት ጊዜ ከእሱ ጋር በዩኒቨርሲቲ ሁለት አፍሪካውያን አብረውት ይማሩ እንደነበሩ ይናገራል፤ እነዚህ አፍሪካውያን የፈረንሳይኛ ቋንቋን ልክ አንደፈረንሳዮች እየተናገሩ፣ እንደፈረንሳዮች እያሰቡ ከፈረንሳዮቹ ተማሪዎች ጋር እኩል በትምህርት እየጎለበቱ ነበር፤ በኋላ እነዚህ አፍሪካውያን ወደአገራቸው ተመልሰው ሥልጣን ላይ ሲወጡ ሰፊ አገራቸው ለሁለቱ የተማሩ አፍሪካውያን የማይበቃ ሆነባቸው፤ ስለዚህም አንደኛው የአገር መሪ ሆነና ሌላውን ገደለው፤ የፈረንሳዩ ፈላስፋን ያሳዘነው ትዝብት ነው።