በእነ ሀብታሙ አያሌው የክስ መዝገብ አንድነት ፓርቲ ያቀረበው ክስ ውድቅ ተደረገ

በዛሬው ዕለት በአራዳ ምድብ ፍታብሔር ችሎት ሀምሌ 8 ቀን 2006 ዓ.ም በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት የማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ የፀረ ሽብር ዲቪዚዮን ኃላፊ ኮማንደር ተክላይ መብራህቱ የእስር ትዕዛዙንና የጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀበትን ሰነድና ታሳሪዎቹን ይዘው እንዲቀርቡ ቢያዝም ኃላፊው ታሳሪዎቹን ሳይዙ ቀረቡ፡፡

ችሎቱ በ4፡30 ተሰይሞ ዳኛው ከሳሽና ተከሳሽ መቅረባቸውን ካረጋገጡ በኋላ እስረኞቹ መቅረባቸውን ዳኛው ጠየቁ፤ ተከሳሽ እስረኞቹን አለማቅረባቸውንና የሰነድ ማስረጃዎቹን ስላቀረብኩ እስረኞቹን እንዳቀርብ አይጠበቅብኝም በማለት ለፍ/ቤቱ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ዳኛው የእስር ማዘዣና የፍርድ ቤት የጊዜ ቀጠሮ ሰነዶች ተከሳሽ ማቅረባቸውን ከገለጹ በኋላ ከሳሾች ያቀረቡት ክስ ውድቅ ሆኗል በማለትይህንን አቤቱታ ለማየት ስልጣን እንደሌለውና ለተከሰሱበት ችሎት አቤቱታችሁን ማቅረብ ነው ያለባችሁ በማለት ክሱ መዘጋቱን ገልጸዋል፡፡10557351_10202411521670248_5400861717310665444_n

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*