ደራሲ መሥፍን ተቀበረ

መስፍን ሐብተማርያም በኢትዮጵያ የመጀመሪያዉ የወግ ፀሐፊ ነበር።በብዙ መቶ የሚቆጠሩ ወጎችን የፃፈና ያሳተመ፤ ተርጓሚ፤ የሥነ-ፅሁፍ ሐያሲ እና አዲስ አበባና አሥመራ ዩኒቭርስቲን ጨምሮ በተለያዩ ተቋማት ያስተማረ የሥነ-ፅሁፍ ሰዉ ነበር።