ፍኖት – የወጣት ሀብታሙ አያሌው ጠበቆች እስረኛዉን እንዳይጎበኙ ተከለከሉ

የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆነው ወጣት ሀብታሙ አያሌው፣ በትላንትናው ዕለት በማዕከላዊ እስር ቤት ከታሰረበት ጊዜ ጀምሮ በቤተሰቦቹ እና በወዳጅ ጓደኞቹ እንዳይጎበኝ በመደረጉ ያለበትን ሁኔታ ለማወቅ እንዳልተቻለ የፓርቲው አመራሮች ለፍኖተ ነፃነት ገልፀዋል፡፡
አመራሮቹ አክለውም፣ በዛሬው ዕለት ወደ ማዕከላዊ እስር ቤት ያመሩት፣ የሀብታሙ ጠበቆች አቶ ተማም አባቡልጉ እና አቶ ገበየሁ እስረኛውን መጠየቅ አትችሉም ተብለው መባረራቸውን አስረድተዋል፡፡