የደቡብ ሱዳን ድርድር በ “ስቱፒድ” ምክንያት ተቋረጠ
የምሥራቅ አፍሪካ ሃገሮች የጋራ ልማት ትብብር ተቋሙ ኢጋድ አንድ ባለሥልጣን በደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር እና በተቃዋሚው መሪ ሪያክ ማሻር ላይ የዘለፋ ቃል ሠንዝረዋል በሚል በሁለቱ ወገኖች መካከል ይካሄድ የነበረው ውይይት ተቋርጧል፡፡
ውይይቱ የተስተጓጎለው ተቃዋሚዎቹ በሰዓቱ ባለመገኘታቸው ጭምር ነው ሲሉ አንድ የመንግሥቱ ቃል አቀባይ የተናገሩ ሲሆን ተቃዋሚዎቹ ደግሞ የተሟላ ውክልና ስለመኖሩ ሥጋት አለን ብለዋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ተቃዋሚዎቹ ባለፈው ዕሁድና በማግስቱም ሰኞ በናስር ከተማ ላይ ጥቃት አድርሰዋል ሲሉ የአፐር ናይል ግዛት ባለሥልጣናት ክስ አሰምተዋል፡፡
ጥቃቱ በደረሰ ወቅት በመረጋጋቱ የተበረታቱ ሰላማዊ ነዋሪዎች ወደ ከተማይቱ እየተመለሱ እንደነበረ ባለሥልጣናቱ አመልክተዋል፡፡
የተቃዋሚዎቹ ቃል አቀባይ ግን…