እስራኤል እና ሐማስ ከስምምነት ለመድረስ ተቃርበዋል፤ የተኩስ አቁም ምንድን ነው? ጦርነትን ያስቆማል?

የባሕረ ሰላጤዋ አገር ኳታር አደራዳራዳሪዎች እንደሚሉት እስራኤል እና ሐማስ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስ ከጫፍ ደርሰዋል። እስራኤል በሐማስ የተፈጸመባትን ድንገተኛ ጥቃት ተከትሎ በጋዛ ላይ እያካሄደችው ያለው መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ዘመቻ 15 ወራትን ሊያስቆጥር በተቃረበበት ጊዜ ነው ሁለቱ ወገኖች ከስምምነት ለመድረስ መቃረባቸው የተነገረው። ለመሆኑ የተኩስ አቁም ስምምነት ምንድን ነው? የተኩስ አቁም ስምምነት ግጭትን በዘላቂነት ያስቆማል? ወይንስ ለተወሰነ ጊዜ ብቻ ፋታን የሚሰጥ ነው?