አቡጊዳ – የሚሊዮኖች ንቅናቄ ሰልፍ በአዳማ/ናዝሬት (ፎቶዎችን ይዘናል)
ዛሬ ሰኔ አንድ ቀን 2006 ዓ.ም በአዳማ/ናዝሬት የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት እና ለፍትህ በሚል መርህ ፣ የተጠራው ሰላማፊ ሰልፍ እጅግ በጣም በደመቀ ሁኔታ መጠናቀቁ ከስፋራዉ በደረሰን ዘገባ ለማወቅ ችለናል። ሰልፉ በሰላም ተጀምሮ በሰላም የተጠነቀቀ ሲሆን፣ በአማርኛ እና በአፋን ኦሮሞ የተለያዩ ቀረርቶዎች ሲሰሙበት እንደነበረም ለማወቅ ችለናል። የተለያዩ መፈክሮች በአማርኛ እና በአፋን ኦሮሞ ሲሰሙ የነበረ ሲሆን፣ የነጻነት ዘፈኖችን በሁለቱ ቋንቋዎች ሕዝቡ እየዘፈነ ሰልፉን በጣም አድምቀዉታል።
«የአሊቢራ ባንድ መጧቷል ወይ ? » እስኪባል ድረስ ሙሲሊሙን ፣ ክርስቲያኑ፣ ኦሮሞዉን፣. አማራዉን ፣ ጉራጌዉን …ድብልቁን ሁሉንም በአንድነት ያሰባሰበው የአዳማዉ ሰልፍ አስደናቂ የሆነ የኢትዮጵያዊነት መንፈስ የታየበት ሰልፍ ከመሆኑም በተጨማሪ ፣ ሕዝቡ ጨዋነቱን ያሳየበት ሰልፍ ነበር። የተወረወረ ጠጠር፣ የተበላሸ ንብረት እንዳልነበረ የደረሰን ዘገባ ገልጾ፣ ሰልፉ በሰላም ተጀምሮ በሰላም ተጠናቋል።
ከአዳማዉ ሰልፍ በተጨማሪ በደብረ ማርቆስም ተመሳሳይ ደማቅ ሰልፍ መደረጉም ይታወቃል።





