ሰማያዊ – የሰማያዊ ፓርቲ የአመራር ሽግሽግ አደረገ

ሰማያዊ ፓርቲ የ2006 ዓ.ም የምክርቤት መደበኛ ስብሰባ የግማሽ አመት የስራ እቅድ ትግበራ ሪፖርትን ገምግሞ ያፀደቀ ሲሆን በሊቀመንበሩ የቀረበለትን የስራ አስፈፃሚዎች ኃላፊነት ሽግሽግም አፅድቋል፡፡

blue_leaders

በመሆኑም አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድ ወደ አደረጃጀት ጉዳይ ሲሄዱ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ደግሞ ከወጣቶች ጉዳይ ወደ ህዝብ ግኑኙነት ኃላፊነት ተዛውረዋል፡፡ የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ በመሆን የተመደበው ደግሞ አቶ እያስፔድ ተስፋዬ ሲሆን የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ የነበሩት አቶ ጌታነህ ባልቻ የጥናትና ስትራቴጂ ክፍል ኃላፊ ሆነዋል፡፡

የፓርቲው ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ሽግሽጉ ወደፊት ልንሰራቸው ላቀድናቸው በርካታ ተግባራት በበለጠ ፍጥነት ለመጓዝ ሲባል ስራ አስፈፃሚዎቹ በተሻለ ልምድ ባካበቱበት እና አቅም በፈጠሩበት የስራ ምድብ በኃላፊነት እንዲሰሩ ሽግሽጉ እንደተደረገ ለምክርቤቱ አስረድተዋል፡፡

የሰማያዊ ፓርቲ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት፡- የሰማያዊ ፓርቲ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት፡-

ሊቀመንበር – ይልቃል ጌትነት (ኢ/ር) / Yilkal Getnet /
ምክትል ሊቀመንበር – ስለሺ ፈይሳ / Sleshi Feysa /
የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ – ብርሃኑ ተ/ያሬድ / Brhanu Tekleyared Ze Ethiopia /
የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ – ዮናታን ተስፋዬ / Yonatan Tesfaye /
የውጭ ግንኙነት ኃላፊ – ሰለሞን ተሰማ / Solo Cima /
የጥናትና ስትራቴጂ ኃላፊ – ጌታነህ ባልቻ / Getaneh Balcha /
የህግ ጉዳይ ኃላፊ – ይድነቃቸው ከበደ / Yidnekachew Kebede /
የፋይናንስ ጉዳይ ኃላፊ – ወረታው ዋሴ / Woretaw Wassie /
የመረጃና ደህንነት ኃላፊ – ዳዊት ዋለልኝ
የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ – ኢያስፔድ ተስፋዬ / Eyasped Tesfaye /
የሴቶች ጉዳይ ኃላፊ – ሀና ዋለልኝ