አቡጊዳ – መኢአድ እና አንድነት ነገ የቅድመ ዉህደት ስምምነት በመኢአድ ጽ/ቤት ይፈርማሉ
የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) እና የመላዉ ኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ነገ ሰኔ አንድ ቀን 2006 ዓ.ም፣ የቅድመ ዉህደት ስምምነት እንደሚፈረም ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ ገለጸ። ፓርቲዎች የነበሯቸዉን ጥቃቅን ልዩነቶች ሁሉ በጋራ የፈቱ ሲሆን፣ በአንድ ወር ጊዜ ዉስጥ ጠቅላላ ጉባኤ ጠርተው ዉህደቱን ለማጠናቀቅ ተስማምተዋል።
ዘዝር ዘገባና የስምምነቱን ሙሉ ሰንድ እንዳገኝን ይፋ እናደርጋለን።