አቡጊዳ – በናዝሬት ቅስቀሳዉን ፖሊሶች ለማስተጓጎል ቢሞክሩ ሕዝቡ በራሪ ወረቀቶች እየደረሱት ነው

በአዳማ ናዝሬት ዛሬ ሐሙስ ግንቦት 28 ቀን ቅስቀሳ ሲደረግ እንደነበረ፣ የአንድነት ፓርቲ የአዳም/ናዝሬት ቅርንጫፍ በፌስቡክ ገጹ ገለጸ። የመኪና ቅስቀሳ እንዳይደረግና በትላልቅ ፖስተሮች ማስተወቂያ እንዳይለጠፍ ፖሊሶች ያከላክሉ የነበሩ ሲሆን በቅስቀሳዉ የተሰማሩ፣ ድሬዳዋ ሆቴል አካባቢ፣ ለሰዓታት ታስረው እንደነበረ የአዳማ/ናዝሬት አንድነት ቅርንጫፍ በፌስ ቡክ ገጹ ያቀረበው ዘገባ ያስረዳል።adama1

የሰልፉን ሕጋዊነት የሚገልጥ ደብዳቤም ቀስቃሾቹ ለፖሊሶች ቢያሳዩም ፖሊሶቹ ለመልቀቅ ፍቃደኛ እንዳልነበሩና ሊለቋቸው እንዳልቻሉ ዘገባው ገልጾ፣ ሕዝብ ግን ከመኪናው ላይ በራሪ ወረቀቶችን እየተሻማ ሲወስድ እንደነበረም አትቷል። በቅስቀሳዉ ወቅት የታሰሩ የአንድነት አባላት ዘጠኝ እንደሆኑ፣ ከነርሱም መካከል የአዳማ/ናዝሬት አንድነት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ ተስፋዬ ዋቅቶላ እነ ሌሎች አማራሮች እንደሚገኙበት ለማወቅ ችለናል።

«በዚህ ሁኔታ ቅሰቀሳቸውን የፀጥታዉ ክፍል ቢያስተጓጉልም፣ ከሰዓት በኋላም ቀጥለዋል፡፡ሆኖም ፖስተር መለጠፍ አትችሉም በማለታቸው ዛሬም አልተለጠፈም፡፡በራሪ ወረቀቱን ቢከለክሉንም አባላቱ በከተማው በመዟዟር ሲበትኑ ውለዋል» ያለው የአዳማ/ናዝሬት አንድነት፣ ቅስቀሳው በነገው እለትም በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥል አስታወቋል።