መለስ ዜናዊ ልምከርህ

መለስ ዜናዊ ልምከርህ
አግባብ አይደለም ቁጣህ
እስቲ ክሊንተን ምንበደለህ
ብላተኛ ነው ያለህ።
ስማኝ ዜናዊ ላውጋህ
አግባብ አይደለም ቁጣህ
አገሬ መቼ ቂም ያዘች
ለናንት ይብላኝ ነው ያለች።
መለስ ዜናዊ ገዣችን
ጨርቅ ነው አለ ሰንደቃችን
ጉም ከልሎት ነው የጉና
የአድዋ ማይጨው ደመና።
በኤደን ባህር በየመን
ኮበለለ አሉ ሰዋችን
ሆድ እንዴት አይብስ አይከፋ
ዘር በያገሩ ሲጠፋ።
አደገች አሉ አገራችን
በወያኔ መሪያችን
ኢትዮጵያውያን በረሩ
በየወጡበት ቀሩ።
ሸራተን ገብተን ስንደንስ
አንተን ይበልህ ደስ ደስ
እድገት ይሄ ነው ያውልህ
ወይም መንገዱን ጨርቅ ያርግልህ
ያለው ዜናዊ ደረሰልኝ
የኔን ዕድል ይስጥልኝ።

በወርቁ ለገሠ (Friday, October 01, 2010)