የከፍተኛ 15 ቀይ ሽብር ተዋንያን ከፍያለኝ ዓለሙ 22 ዓመት እሥራት ተፈረደበት – ከ«ያ ትውልድ ተቋም» የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

የከበረ ሰላምታችንን በቅድሚያ አያቀረብን፤
May 23, 2014 (ግንቦት ፲፭ ቀን ፪ ሺህ ፮ ዓ.ም.) በሰሜን አሜሪካ ዴንቨር ኮሎራዶ የአረመኔውን ከፍተኛ 15ቱ ቀይ ሽብር ተሳታፊ ከፋለኝ ዓለሙን ጉዳይ የመጨረሻ ፍርድ ውሳኔ ለመስጠት የፍርድ ቤቱ ችሎት ከጠዋቱ 9፡30 ተሰየመ። ጉዳዩን ሲከታተል የነበሩት ጠበቆችና የሚመለከታቸው ተገኝተዋል። ከፋለኝ ዓለሙን ለመጀመሪያ ጊዜ በዴንቨር ኮልራዶ በመመልከት ወደ ፍርድ ይቀርብ ዘንድ ከፍተኛውን ድርሻና ኃሊፊነት የተወጣው የዴንቨሩ ነዋሪ አቶ ክፍለ ከተማን ጨምሮ በነሀሴ ፬ ቀን ፪ ሺህ ፭ ዓ.ም. በዳንቨር በተካሄዯው የፍርድ ቤት ውል በአካል በመገኘት በከፋለኝ ዓለሙ በከፍተኛ 15 እሥር ቤት በ1970/71 ዓ.ም. በጊዜው ወጣቶች፣ ሕፃናትና አዛውንቶች ሊይ የፈጸመውን አሰቃቂ ግርፋት፣ ግፍና ግዴያ በመመስከር ተገኝተው የነበሩት ወ/ሮ አበበች ደምሴ ከሳንሆዜ፣ አቶ ብርሃን ዲርጌ ከዋሽንግተን ዱሲ፣ ዶ/ር ሳሙኤል ከተማ ከዳንቨር እና አቶ ነሲቡ ስብሏት ከቨርጂንያ ሲገኙ አቶ አሳየኸኝ ፈለቀ ከቦስተን በሥራ ምክንያት አልተገኙም። በፍርድ ሂደቱ የከፋሇኝን ጉዲይ የያዙት ጠበቃ ከፋለኝ ዓለሙ የአሜሪካንን መንግስት በማጭበርበር ባደረገው ማንነትን የማታለሌ ጉዳይ የ22 ዓመት እስራት እንደሚገባው ፍርድ ቤቱን ጠየቁ። የፍርድ ቤቱ ዲኛ ጉዲዩን ከተለያየ አቅጣጫ ካደመጡና ከተመለከቱ በኋላ በዛሬው ዕለት በከፋለኝ ዓለሙ ሊይ የ22 ዓመት እስራት ብያኔ ሰጥተዋል።

ነሏሴ ፲፰ ቀን ፪ ሺህ ፬ ዓ.ም. (August 24, 2012) ከፍለሇኝ ዓለሙ በሰሜን አሜሪካ ዳንቨር ኮልራድ የአሜሪካን ደህንነት ኃይሎች ቁጥጥር ሥር በመዋል ወደ እስር ቤት መግባቱ ይታወቃሌ። የከፋለኝ ዓለሙን ጉዳይ ሳትሰለቹ በመከታተል እዚህ ለደረሳችሁና የመጨረሻውን ብይን ሊሰጣችሁ የከፍተኛ 15 ወገኖችና የያ ትውልድ አባሊት ምስጋናችን ይደረሳችሁ። እናመሰግናለን። የያ ትውልድ አባላትና የቀይሽብር ቀጥተኛ ተጠቂ ወገኖችና ቤተሰቦች በመላ እንኳን ደስ አላችሁ። በአድራጏቱና በአረመኔነቱ ተወዳዳሪ የማይገኝለት ይህ ግለሰብ፡ በትዕቢት ያፈሰሰው የንጹሃን ወንድምና እህቶቻችን ደም፤ ዛሬ ከ36 ዓመት በኋሊ ተፋራጅና ተሟጋች በማግኘት ከፍያለኝዓለሙን ለፍርድ በማቅረብ የመጨረሻውን ብይን እንዱያገኝ ተደርጓል። የያ ትውልድሰማዕታትን ጨምሮ የከፍተኛ 15ቶቹ ብርዬ ሀ/ማርያም፣ ክፍላ ቄስ፣ ታዯሰ ቢፍቱ፣ ግዛው ወረሳ፣ አፈሳ በቀሇ፣ በዛ ገ/ሕይወት፣ አሸናፊ በቀሇ፣ አሰሇፈች፣ ሶፊያ አየለ፣ ዮሏንስ ስዩም፣ ዳንኤል አንጋጋው ወዘተ እና የበርካታ ወጣቶች ዯም ምንጊዜም ቢሆን ተፋራጅ እንዲሇው እንረዲሇን። የበርካታ ወጣቶችንና ጎሌማሶችን ዯም እንዯውሃ አፍስሦ ምንም እንዲሌሰሩ አዴፍጦ መቀመጥና ይባስ ብል ያንን ትውሌዴ ተጠያቂ ለማዴረግ የሚደረገው ሩጫና ታሪክ ብረዛ ተከላካይና ሀቁን አስረጂ ወገን እንዳለው ጥርጣሬ የሚገባን አይመስለንም። ጊዜው ምን ቢርቅ ታሪካችን ተዳፍኖ እንደማይቀመጥና ለትውልድ እንደሚተላለፍ የምናደርገው ጥረት ፍሬ እንደሚያሳይ በያ ትውልድ ስም እያደረግን ያለው እንቅስቃሴ ውጤት መስካሪ መሆኑን «ያ ትውልድ ተቋም» ያምናል።

የከፍተኛ 15ን ቀይ ሽብር ተሳታፊ ከፍያለኝ ዓለሙ ያለበት ቦታ ከታወቀ ጀምሮ ጉዲዩን በመከታተሌ ሙለ ትብብርና ድጋፍ ላደረጋችሁ ሁሉ ልናመሰግን እንወዲለን። በተለይ ከፍያለኝ ዓለሙ የዛሬ 36 ዓመት የሰራውን ወንጀሌ የምታውቁትንና ያያችሁትን ለመመስከር ምንም ሳታወላውሉ ፈቃደኛ በመሆን ለተባበራችሁ ዛሬ ከፍያለኝ ዓለሙ ማንነቱ እንዱታወቅ ፍርድ ማለት ምን እንደሆነ ይመለከት ዘንድ ያበረከታችሁት አስተዋጽዎ ውጤት ነውና በሰማህታት ወንድምና እህቶቻችን ስም ከ«ያ ትውልድ ተቋም» ምስጋችን ይድረሳችሁ።
በከፍተኛ 15 ለምትገኙ በደርግ ያንድ ትውልድ መመተር ቀይ ሽብር ጥቃት ሰሇባ ለሆናችሁ ቤተሰቦችና ወገኖች በሞላ፡ የዛሬ 36 ዓመት በማንሃህልኝነት በየእሥር ቤቱና በየመንገደ የፈሰሰው የልጆቻችሁ ደም ሰሚ ሊያገኝ ችሏል። ጊዜው ምንም ቢርቅ ጉዲዩ ዛሬም ያንገበግባልና ወንጀላቸውን ተሸክመው ማንነታቸውን ደብቀውና አድፍጠው ያለ መሰሌ ከፋለኝ ዓለሙ ገዳዮች ምንጊዜም፣ ዛሬም ወደ ሕግ መቅረቡ ለሌሎች ትምህርት ሊሰጥ ይገባዋል እንላለን። ጊዜ የሰጠውን ጉልበትና ኃይል ተጠቅሞ ያለአግባብ የሚፈስ የንጹኋን ደም ሌላ ጊዜ የፍትህ ያለህ ብሎ ወደ ሕግ እንደሚያቀርበው ትምህርት ሊወሰድበት ይገባል። ዛሬ ዓለም የወንጀለኞችና የገዳዮች ዋሻ አለመሆኗን በትንሹም ቢሆን ግንዛቤ እንድንወስድ ይገባል እንላለ።
በ1969/70/71 ዎቹ የደርግ ቀይሽብር ተሳታፊዎች ጉዳይ የሁላችንም የያ ትውልድ አባላትና ቤተሰቦች የጋራ ኃላፊነት ነው ብለን እናምናለን። በመሆኑም በየቦታው አድፍጠው የተቀመጡትን በደም የተነከሩ ወንጀለኞች ቢያንስ በኅብረተሰቡ ሊታወቁ የሚገባቸው በመሆኑ የጉዳዩ ባለቤት ሁላችንም ነንና፤ ድጋፍና ትብብራችን ለግለሰቦችና ለተወሰኑ አካላት ሳይሆን ለሚነሳውና ለተነሳው ጉዳይ መሆኑን በማገናዘብ ድምጻችንን በጋራ እናሰማ እንላለን።

«ያ ትውልድ ተቋም» ከፋለኝ ዓለሙን ለፍርድ ለማቅረብ የሚደረገውን ሂደት ሙሉ ድጋፍ በመስጠት እንደተባበረን ሁሉ በቀጣይነትም በየቦታው አድፍጠው የተቀመጡ የደርግ ቀይ ሽብር ተሳታፊዎችን ከያለበት በማውጣት ሕዝብ እንዱያውቃቸው ማድረግ ይጠበቅብናልና እንተባበር እንላለን።
እናመሰግናለን
“ያ ትውልድ” ተቋም10325604_647372802010223_9214526956955649190_n