ሚኒሊክ ሳልሳዊ – ወለጋ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አደጋ ውስጥ ናቸው
ካድሬዎች ወጣቶቹን እያደራጁ በአማርኛ ተናጋሪዎች ላይ ግድያና ድብደባ እንዲፈጽሙ እያደረጉ ነው፡፡ ትናንትና ማታ የኦህዴድ ካድሬዎች ቤታቸውን በእሳት ሲያቃጥሉባቸው አምሽተዋል፡፡ ህጻናት ሳይቀር ተቃጥለዋል፡፡
አብዛኛዎቹ ከተደበቁበትና ቤታቸው ያልተቃጠለባቸውም ከሰፈራቸው ለመውጣት አልቻሉም፡፡ በርካቶቹ ተደብቀው በምግብ እጦት ላይ ናቸው፡፡ ካድሬዎች አስረኛ እና አስራ ሁለተኛ ክፍል ያቋረጡ ወጣቶቹን እያደራጁ በአማርኛ ተናጋሪዎች ላይ ግድያና ድብደባ እንዲፈጽሙ እያደረጉ ነው፡፡ ወጣቶቹ ከከተማ በመውጣት ኦሮምኛ ተናጋሪ አርሶ አደሮችን በመቀስቀስ በአማርኛ ተናጋሪዎቹ ላይ ይዘምታሉ፡፡ በዚህም በርካታ ሰዎች የሞቱ ሲሆን እጅግ በርካቶች ቆስለዋል፡፡ በከተሞች የሚገኙ ሱቆች፣ መጋዘኖችና ሌሎች የንግድ ቤቶች ተቃጥለዋል፡፡ ፈርሰዋል፡፡