አቡጊዳ – አምቦ ወድማለች- ብዙዎች ተገድለዋል፤ ብዙዎች በፍርሃት ላይ ናቸው ! (ፎቶዎች ይዘናል)
ጥንታዊቷ የአምቦ ከተማ ፣ የኢትዮጵያን ዋና ከተማ አዲስ አበባ ከምእራቡ የኢትዮጵያ ክፍል የምታገናኝ ከተማ ናት። አገዛዙ በሚወስዳቸው ዘረኛ ፖሊሶዎች ምክንያት፣ አምቦ ብዙ የተረሳችና ሰፋፊ የልምታ እንቅስቃሴዎች የማይታዩባት ከተማ ነበረች። በከተማዋ ሶስት ፎቆች ብቻ የነበሩ ሲሆን፣ አገዛዙከፍተኛ አፈና ከሚያደርግባቸው ቦታዎች አንዷ ነበረች።
ሰሞኑን በተነሳው ረብሻ ብዙዎች የተገደሉ ሲሆን፣ በከተማዋ የነበሩ ሶስት ትላልቅ ፎቆች ወድመዋል። የወ/ር አበበች ኢንተርናሽናል ሆቴል፣ የወ/ር ማርታ ሌላ ትልቅ ሞደርን ሆቴል እንድሁም አንድ ትልቅ ባንክ ወድመዋል።
በከተማዋ የሚኖሩ፣ ኦሮሞ ያልሆኑ ከ አንድ ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎች ፣ ከአክራሪ ኦሮሞዎች ጥቃት ለመዳን፣ በየ ቤተ ክርስቲያናቱ ተደብቀው የነበረ ሲሆን፣ አሁንም በስጋትና በፍርህታ ላይ እንዳሉ ዘገባዎች ይጠቁማሉ።
በአምቦ ሕይወታቸው የተቀጠፉ ጥቂቶችን ፣ እንዲሁም የነበረዉን የንብረት ዉድመት የሚያሳይ ፎቶዎች ይመለክቱ






