የአዲስ አበባ – አዳማ የፍጥነት መንገድ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ።
ከ 11 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የሆነበት መንገድ ከአዲስ አበባ ናዝሬት/አዳማ በ45 ደቆቃዎች ዉስጥ ብቻ እንዲደርስ የሚያደርግ ሲሆን ፣ ሁለቱንም ከተሞች በኢኮኖሚም ሆነ በሌሎች ማህበራዊ ዘርፎች የሚያገናኝ ነው። ከናዝሬት አዲስ አበበ ለመሄድ ከሁለት ሰዓታት በላይ ይፈጅ እንደነበረ ይታወቃል።

የዚህ መንገድ መሰራት ዜጎችን ናዝሬት እየኖሩ አዲስ አበባ እንዲሰሩ፣ አዲስ አበባ እየኖሩ ናዝሬት እንዲሰሩ የሚያስችል ሲሆን በናዝሬት እና አዲስ አበባ መሃክል ያሉ ትናንሽ ከተሞችና መንደሮችን በሰፋት የሚጠቅም ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።