ደቡብ ሱዳን፡- ተመድ “አስፈላጊ እርምጃ” እንዲወስድ ባን ጠየቁ
ደቡብ ሱዳን ውስጥ ከእንግዲህ የሰላሙን ሂደት የማፋጠን ሥራ የፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር እና የአማፂው መሪ ሪያክ ማሻር ጉዳይ ነው ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ባን ኪ ሙን አሳሰቡ፡፡
ሚስተር ባን ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ትናንት ያደረጉት ንግግር ለወራት የዘለቀውን ጦርነት ለማስቆምና አዲስ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ከተስማሙ በጥቂት ቀናት ውስጥ ቢሆንም የስምምነቱ መጣስ ወሬና የሃገሪቱ ዜጎች የሚገኙበት ሁኔታ በእጅጉ እያሳሰባቸው መሆኑን አመልክተዋል፡፡
ዋና ፀሐፊው ባለፈው ሣምንት ውስጥ ወደ ጁባ ተጉዘው ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪርን አነጋግረል፤ ሃያ ሺህ ተፈናቃዮች የተጠለሉበትን የመንግሥታቱ ድርጅት ግቢንም ጎብኝተዋል፡፡
ተፈናቃዮቹ በመጠለያው ውስጥ እየገፉ ያሉት ሕይወት በእጅጉ ያሳዘናቸው መሆኑን የገለፁት…