አቡጊዳ – በጊድሎ ሕዝቡ በነቂስ ይውጥል ተብሎ ይጠበቃል – (ፎቶዎች ይዘናል)
አንድነት በደራሼ ወረዳ በጊዶሌ ከተማ ለሚያደርገው ሰላማዊ ሰልፍ እውቅና አማግኘቱን ለማረጋገጥ ችለናል።፡ የፊታችን እሁድ ሚያዚያ 29 ቀን ለሚረርገው ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ የክልሉ አስተዳደር እውቅና መስጠቱን ተከትሎ በሰላማዊ ሰልፉ የወረዳውና የአካባቢው ነዋሪ እየደረሰበት የሚገኘውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት፣የመልካም አስተዳደር እጦትና የካድሬዎች ጭቆናን በይፋ የሚቃወምበት እንደሚሆን ፓርቲው አስታውቋል፡፡
በ2002 የደራሼ ወረዳ ሕዝብ በራሱ አነሳሽነት ሰልፍ ወጥቶ የነበረ ሲሆን፣ በወቅቱ የነበረዉን ሰልፍ የሚያሳይ ፎቶም ከታች አቅርበናል። በርካታ ሕዝብ ድምጹን ያሰማበት ሰላምዊ ሰልፍ ላይ የኢትዮጵያ ንጹኋ አረንጓደ ቢጫ ቀን ሰንደቅ አላም ስትዉለበልብ ለመመለክትም ችለናል።




