አቶ አንዷለም አራጌ በቃሊቲ እስር ቤት የረሃብ አድማ ላይ ነው፤ በቃሊቲና በዝዋይ የሚገኙ ታሳሪዎች የርሀብ አድማ ሊያደርጉ ነው!! ለሕዝቡም ጥሪ አስተላልፈዋል! -ፍኖተ ነፃነት-

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ም/ሊቀመንበርና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበረውና ‹‹ሽብርተኛ›› በሚል የእድሜ ልክ እስራት የተፈረደበት አቶ አንዷለም አራጌ በቃሊቲ እስር ቤት ከሌሎች እስረኞች በተለየ ሁኔታ እሱ ላይ ብቻ ትኩረት ተደርጎ መብቱ በመጣሱ፤ እንዲሁም በተፅእኖና ክልከላ ሰለባ በመሆኑ ከትላንት ጀምሮ የረሃብ አድማ ላይ መሆኑን ቃሊቲ የሚገኙ የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ገለጹ፡፡

በቃሊቲና በዝዋይ ማረሚያ ቤቶች በግፍ ተፈርዶባቸው በእስር ላይ የሚገኙ የህሊናና የፖለቲካ እስረኞች አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ‹‹የእሪታ ቀን ›› በሚል መሪ ቃል የሰየመውና እሁድ ሚያዝያ 26 ቀን 2006 ዓ.ም የጠራውን ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ በማስመልከት ከህዝብ ጎን ሆነን ድምፃችንን እንዳናሰማ በግፍ የተወረወርንበት እስር ቤት ቢያግደንም ከአርብ ጀምሮ ሰላማዊ ሰልፍ እስከሚደረግበት እለት ድረስ የርሀብ አድማ በማድረግ ከህዝቡ ትግል ጎን በመቆም አጋርነታችንን እናሳያለን ሲሉ ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡ ህዝቡ ከየቤቱ በነቂስ በመውጣት ሰላማዊ ሰልፉን እንዲቀላቀልም ጥሪ አቅርበዋል፡፡1554590_628565093895095_9136488348360005387_n

aacarudj3

images