የአንድነት አዲስ አበባ ምክር ቤት ሰብሳቢና ጋዜጠኛ ነብዩን ጨምሮ 11 አባላት ታሰሩ – ቅስቀሳዉ ግን ቀጥሏል

የአዲስ አበባ አስተዳደር እውቅና የሰጠውን የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ የአዲስ አበባ ፖሊስ የቅስቀሳ ቡድኑን በማሰር ቅስቀሳውን ለማስተጓጎል እየሞከረ እንደሆነ በስፋት እየተዘገበ ነው።፡ቅስቀሳው ከጽ/ቤት ተነስቶ በ4ኪሎ አሚሪካ አምባሲ፣ መነን ት/ቤት፣ አፍንጮ በር፣ ፒያሣ፣ ቸርቸር ጎዳና፣ ጥቁር አንበሳ፣ ፍልውሃ፣ ቤተመንግስት፣ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

አቶ ዘካሪያስ የማነ ብርሃን፣ ዘላለም ደበበ፣ ነብዩ ኃይሉ፣ ነፃነት ዘገየ የሚገኙበትን ቡድን «ወረቀት እንድትበትኑ እንጂ የመኪና ቅስቀሳ እንድታደርጉ አይደለም» በሚል ካዛንቺስ በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ እንዲታሰሩ የፖሊስ ጣቢያው ኮማንደር ማዘዙን ለማወቅ ተችሏል። «ቤተ መንግስት አካባቢ ቀስቅሳችኋል» እያሏቸውም ነው።

ብሮሸርና ፍላየር የሚያሰራጩ ወደ ቦሌ የተጓዙ አባላት መሳይ ትኩ፣ ማቲዎስ አርጉና አያሌው ዳርምያለውን ጃፓን ኤምባሲ (ጤና ጣቢያው) አካባቢ ባለው ፖሊስ ጣቢያ ታግተዋል፡፡

ወደ ጎተራ ለመኪና ቅስቀሳ የተንቀሳቀሰው ቡድን አባላት ካሣሁን ገ/ሚካኤል፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ ኤፍሬም ሰለሞንና አሸናፊ አሳመረውን ጎተራ ፔፕሲ አካባቢ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ታግተዋል።
አቶ ዘካርያስ የማነአብ ሰልፉ ያዘጋጀው የአዲስ አበባ የአንድነት ምክር ቤት ሊቀመነበር ሲሆን፣ ነብዩ ኃይሉ ደግሞ የፍኖት ነጻነት ዋና አዘጋጅ ነው።

የፓርቲው ከፍተኛ አመራር አባላት አስተዳደሩ ለሰልፉ የሰጠዉን የ እውቅና ደብዳቤ በማስየት ፣ የፖሊስ ድርጊት ሕግ ወጥና የሚይስጠይቅ መሆኑን በመገልጽ እስረኞችን ለማስፈታት እየሞከሩ ነው።
የአንድነት ፓርቲ በሃያ ሶስቱም ወረዳዎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ቀሳቅሾችን ያሰማራ ሲሆን፣ ከአንድ መቶ አምሳ ሺህ በላይ በራሪ ወረቀቶች መታደላቸውንም ለማረጋገት ችለናል።
የአዲስ አበባ ነዋሪም «እሁድ እንወጣለን አይዟችሁ በርቱ» በማለት ቀስቃሾቹን እያበረታቱ እንደሆነ ከስፍራኡ የደረሰን ዜና ያመለክታል።

aaudjpriso1

aaudjpris2

aaudjpris3

aaudj_pri1

aaudjpris4

aaudjpri5